#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ በተመረጡ የመንግስት መስሪያ ቤቶች #ቅዳሜ እና #እሁድን ጨምሮ #በበዓላት ቀናት መስራት ግዴታ ሊደረግ መሆኑን ተዘግቧል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ፤ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ ፤ " የአገልግሎት መስጫ ጊዜን በተመለከተ አዲስ አበባ ላይ የተለየ ትኩረት ይፈልጋል የሚል እምነት አለን " ማለታቸውን ዘግቧል።

በከተማው የ24 ሰዓት አገልግሎት መስጠት የሚያስችል አቅም መፈጠር አለበት ብለዋል።

አቶ ጥራቱ የቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም የበዓላት ቀን አገልግሎት በአሰራር ተዘርግቶ መተግበር አለበት ሲሉ አስገንዝበዋል።

እንደ ከተማ አስተዳደር ከመደበኛዉ 8 ሰዓት ተጨማሪ መስራት ያለባቸዉ መስሪያ ቤቶች የትኞቹ ናቸዉ ? የሚለዉ ላይ ጥናት እየተደረገ መሆኑን አሳውቀዋል።

በከተማዋ ባለዉ የትራንስፖርት መጨናነቅ እና በተለያዩ ጉዳዮች ሰራተኛዉ ቢሮ ገብቶ የሚሰራበት ሰዓት ዉስን በመሆኑ ሰዉ ማግኘት ያለበትን ተገቢዉን አገልግሎት እንዲያገኝ ለማድረግ የ24 ሰዓት አገልግሎት መስጠት መጀመር አስፈላጊ መሆኑን ማንሳታቸውን የሬድዮ ጣቢያው ዘገባ ያሳያል።

@tikvahethiopia