#SUDAN

ሱዳን ውስጥ እየተደረገ ያለው ግጭት መቀጠሉን ለማወቅ ተችሏል።

በተለይም በዋናነት በካርቱም ሰሜናዊ አቅጣጫ ግጭት እየተካሄደ እንደሆነ ተሰምቷል።

ከትላንት አንስቶ በነበረው ግጭት የሟቾች እና የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ይገኛል። እስካሁን ባለው 56 ሰላማዊ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።

የፈጣን ድጋፍ ሰጭ ኃይሎች በፖርት ሱዳን ጦራቸው #ከውጭ_አውሮፕላኖች ጥቃት እንደረሰበት ገልጸዋል። እነዚህ የውጭ ኃይሎች እነማን እንደሆኑ በግልፅ አልተነገረም።

የውጭ ኃይሎች ከጣልቃ ገብነት እራሳቸውን እንዲያርቁ እና እጃቸውን እንዲሰበስቡ RSF አስጠንቅቋል።

የሱዳን ጦር በRSF ይዞታዎች ላይ የአየር ላይ የቦንብ ጥቃቶችን ስለማድረሱ ለመስማት ተችሏል። ዋና ዋና የሚባሉትን የጦር ሰፈሮችንም መቆጣጠሩ እየተነገረ ነው።

የRSF አዛዥ ጀነራል መሐመድ ሀምዳን ደጋሎ ለሚዲያ በሰጡት ቃል ፤ እስካሁን ከ "አል-ቡርሃን" ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌላቸው ገልጸዋል። " አል-ቡርሃን ተከቧል " ያሉት ዳጋሎ " ያለው አማራጭ እጅ መስጠት ብቻ ነው " ብለዋል።

ሱዳን ውስጥ የምትገኙ ቤተሰቦቻችን ነገሮች እስኪረጋጉ እራሳችሁን እንድትጠብቁ የሚወጡ ትዕዛዞችንም እንድትፈፅሙ አደራ እንላችኃለን።

ቪድዮ ፦ በሱዳን ከተማ ውስጥ ሲቪል ሰዎች በሚኖሩባቸው አካባቢዎች የሚደረጉ ከፍተኛ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን ያሳያሉ።

@tikvahethiopia