#Update

የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ዶክተር ይልቃል ከፋለ ፤ የአማራ ልዩ ኃይልን በተለየ መንገድ ትጥቅ ለማስፈታት እና ለመበተን የተወሰነ ውሳኔ የለም አሉ።

ይህን ያሉት ዛሬ በሰጡት መግለጫ ነው።

ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ምን አሉ ?

- በሀገር ደረጃ በሁሉም ክልሎች የሚገኙ ልዩ ኃይሎችን በፌዴራል የፀጥታ ተቋማት ለማደራጀት ተወስኖ ወደ ትግበራ ተገብቷል።

- ውሳኔው በፌዴራል መንግሥት እና በክልል መንግሥታት ስምምነት የተወሰነ ሲሆን በሁሉም ክልሎች ተግባራዊ ይደረጋል።

- በአማራ ክልል ውሳኔውን ለመተግበር እየተሠራ ነው። ይህንን በተመለከተ ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር ተወይይተናል።

- በአፈጻጸም ላይ በታየ ክፍተት እና በተነዛው ፕሮፖጋንዳ ችግሮች ተከስተዋል። ችግር እንኳን ቢኖር ተወያይቶ መፍታት ይቻላል።

- አብዛኛው የልዩ ኃይል አባል ውይይቱን አጠናቆ ውሳኔውን በካምፕ ሆኖ እየተጠባበቀ ነው።

- ልዩ ኃይሉ ትጥቅ የሚፈታና የሚበተን አይደለም ፤ በላቀ አደረጃጃት ኃላፊነቱን እንዲወጣ የሚያስችል ነው።

- ልዩ ኃይሉ ዓላማውን ተገንዝቦ ለበለጠ ተልእኮ ሊዘጋጅ ይገባል።

- የአማራ ሕዝብ በሁኔታው #ቅሬታ ውስጥ ገብቷል።ቅሬታው የመነጨው በተሟላ መንገድ ለሕዝቡ መረጃ ባለመድረሱ ነው።

- አደረጃጀቱ የሚደገፍ፣ ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያለው የሀገርን አንድነት የሚያረጋግጥ ነው።

- አደረጃጀቱ የአማራን ክልል በተለየ መንገድ የሚጎዳ አይደለም።

- የአማራ ክልልን ልዩ ኃይል በተለየ መንገድ ትጥቅ ለማስፈታት እና ለመበተን የታለመ ዓላማ የለም።

- በተፈጠረ የመረጃ ክፍተት በአንዳንድ ከተሞች የሰላማዊ ሰልፍ እንቅስቃሴ፣ የአድማ ጥሪ እና የሰዎች እና የተሸከርካሪዎች እንቅስቃሴን የመገደብ አዝማሚያዎች እያታዩ ናቸው። አላስፈላጊ አካሄዶች አውዳሚ እና አክሳሪ እንጂ አትራፊ አይደሉም።

- የአማራ ክልል በጦርነት የከረመ ክልል ነው ፤ በጦርነቱ ምክንያት ሕዝቡ ተጎሳቁሏል፣ በጦርነቱ ምክንያት የተጎዳው ኅብረተሰብ እና መሠረተ ልማት ገና ማገገም አልቻለም ፤ ከአንደኛው ችግር ሳናገግም ወደ ሌላ ችግር መሸጋገር ሕዝቡን መጉዳት ነው።

- በመወያየት አላስፈላጊ ጉዳዮችን ማስቆም ይቻላል ፤ ሁሉም አውዳሚ የሆነውን ጉዳይ መከላከል ይገባዋል።

- ግጭት እንዳይፈጠር ወጣቶች እና የሃይማኖት አባቶች የሚመሰገን ሥራ እየሠሩ ናቸው።

- የአማራ ክልል ሕዝብ ጉዳዩን በውል በማጤን፣ በመመካከር እና ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት አስቀድሞ በማሰብ ማስከን ይገባል።

- የአማራ ልዩ ኃይል በተለየ መንገድ የሚጎዳ ውሳኔ አልተወሰነም፣ ወጥና ሀገራዊ ውሳኔ ነው የተደረገው፣ በሁሉም ክልል የሚፈጸም ነው፣ ውሳኔው ለሀገር ግንባታ ታላቅ አስተዋጽዖ አለው።

- ከወቅታዊ ጉዳይ አንጻር የሚነሳው ጥያቄ ትክክል ቢሆንም አፈጻጸሙ ለሀገር የሚጠቅም መሆኑን መገንዘብ ይገባል።

- ከካምፕ የወጡ የልዩ ኃይል አባላት እንዲመለሱ ማድረግ ይገባል።

- የአማራ ሕዝብ ጉዳዩን በሰከነ መንገድ ማየት አለበት ፤ ችግሩ ዳር ወጥቶ ግጭት እንዳይከሰት እያደረጉ ላሉ አካላት ምስጋና ይገባል።

- የልዩ ኃይል አባላት ትጥቅ አትፈቱም፣ የምትበተኑበት ነገር የለም፣ ወደ ላቀ ተልእኮ ነው የምትሸጋገሩት።

- በመደማመጥ ችግሮቻችን እንፈታለን፣ የአማራን ጥያቄዎች እናስመልሳለን።

#AMC

@tikvahethiopia