#ሶማሊያ #ኢትዮጵያ #ኤርትራ

የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሐሰን ሼይክ መሐሙድ " የሶማልያ እና የኢትዮጵያን የሁለትዮሽ ግንኙነት እና ስልታዊ አጋርነት ለማጠናከር ቁርጠኛ ነኝ " ሲሉ አሳውቀዋል።

ፕሬዝደንቱ ይህን የገለጹት ዛሬ በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር ሞሐመድ ዋሬ የሹመት ደብዳቤ በተቀበሉበት ወቅት እንደሆነ የሶማሊያ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።

ፕሬዝደንት ሐሰን ሼይክ መሐሙድ ዛሬ የአምባሳደሩን የሹመት ደብዳቤ የተቀበሉት ለሥራ ጉብኝት ከተጓዙበት አስመራ ወደ ሞቃዲሾ ከተመለሱ በኃላ ነው።

ፕሬዝደንቱ በአስመራ ከኤርትራው አቻቸው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ተገናኝተው መወያየታቸው ታውቋል።

ውይይቱ " የጋራ ጠቀሜታ ባላቸው የቀጠናዊ ጉዳዮች " ላይ እንደነበረ የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል መናገራቸውን ዶቼ ቨለ ዘግቧል።

የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ወደ ስልጣን ከመጡ በኃላ ለስራ ጉብኝት ወደ ኤርትራ በተደጋጋሚ ጊዜ መጓዛቸው ይታወቃል።

@tikvahethiopia