#ትኩረት

በምስራቅ ሀረርጌ  ዞን የተከሰተው ድርቅ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የኢትዮጵያ ህጻናት አድን ድርጅት አስታወቀ፡፡

ድርጅቱ በዞኑ ውሃ ፤ የጤናና ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶች በአፋጣኝ እንደሚያስፈልጉ አሳውቋል።

የኢትዬጵያ ህጻናት አድን ድርጅት የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የሚዲያ ዘርፍ ዳይሬክተር አቶ አብዱራዛቅ አህመድ  " የተከተሰው ድርቅ ከፍተኛ ችግር እያስከተለ በመሆኑ በ35 ወረዳዎች ላይ ድጋፍ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ናቸው " ብለዋል።

ድርጅቱ ከ2 መቶ በላይ ትምህርት ቤቶች ላይ ለተማሪዎች  ምገባ እያደረገ መሆኑን አሳውቀዋል።

በድርቁ ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን የገለፁት ዳይሬክተሩ በድርቁ ከ2 ሚሊየን በላይ እንስሳት እስካሁን መሞታቸውን አንስተዋል፡፡

ቦረና ላይ ከተከሰተው ድርቅ ባልተናነሰ በምስራቅ ሀረርጌም በዜጎች እና በእንስሳት ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን ገልጸው በዚህ ምክንያት ግን እስካሁን የሞተ ሰው ስለመኖሩ ያገኙት መረጃ እንደሌለ ተናግረዋል፡፡

ድርቁ ነአርሶ አደሩ ላይ ከፍተኛ ጫና እንደፈጠረ የተናገሩት ዳይሬክተሩ ዝናብ ካልዘነበ አሁንም በዞኑ ያለው ችግሩ እየተባባሰ እንደሚመጣ አመልክተዋል።

በዞኑ ካለው ችግር፤ አንፃር የሚደርሰው እርዳታ ተመጣጣኝ እንዳልሆነ አመልክተዋል።

በሌላ በኩል ፤ ድርጅቱ ቦረና ላይ ለደረሰው ድርቅ እርዳታ ተደራሽ ለማድረግ ድጋፎችን እያሰባሰበ መሆኑን አሳውቀዋል።

Credit : አሀዱ ሬድዮ እና ቴሌቪዥን

@tikvahethiopia