#ሶማሌላንድ

በሶማሌላንድ ግዛት በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎችና በተቃዋሚ ኃይሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት በርከታ ሰዎች ሰላም ፍለጋ ወደ #ኢትዮጵያ እየገቡ ናቸው።

እስካሁን ግጭት የሸሹ ከ83 ሺ በላይ የሶማሌላንድ ነዋሪዎች ወደ ኢትዮጵያ ድንበር በመዝለቅ በሶማሌ ክልል መስፈራቸው ተነግሯል።

የተመድ የስደተኞች ኮሚሽንን ዋቢ በማድረግ #ሪፖርተር ጋዜጣ እንዳስነበበው "ላስካኑድ" በምትባለው ከተማ በተከሰተው ግጭት፣ የበርካታ የሶማሌላንድ ነዋሪዎችን ሕይወት የተቀጠፈ ሲሆን በርካታ ሴቶችና ሕፃናት ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል፤ ዶሎ ዞን እየገቡ ናቸው።

እንደ ኮሚሽኑ መረጃ ፦

- እስከ  ቅዳሜ የካቲት 11 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ 14 ሺሕ የሚሆኑ አዳዲስ አባወራዎች (ወይም 83 ሺሕ ግለሰብ ስደተኞች) ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል።

- ስደተኞቹ በዶሎ ዞን፤ ቦህ፣ ገልሃሙርና ዳኖድ በተባሉ 3 ወረዳዎች ተጠልለው ይገኛሉ።

- አብዛኞቹ ስደተኞች ባለፈው ሳምንት ነው ወደ ኢትዮጵያ የገቡት።

- ስደተኞች በ3 ወረዳዎች በ13 ቦታዎች ሠፍረው የሚገኙ ሲሆን የተወሰኑት በትምህርት ቤትና መሰል የሕዝብ መገልገያ ሥፍራዎች ላይ ተጠልለዋል፤ ሌሎች ደግሞ ያለ መጠለያ ሜዳ ላይ ይገኛሉ።

- ከሶማሌ ክልል የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ቢሮ ጋር በመሆን ከ1,500 በላይ ለሆኑ በከፍተኛ ሁኔታ ለተጎዱ አባዎራዎች የተለያዩ ቁሳቁሶችና መሰል ድጋፎችን እየተሰጠ ነው።  ለተጨማሪ 9 ሺህ አባዎራዎች በቀጣይ ቀናት ድጋፍ ይደረጋል።

የሶማሌ ክልል፤ የስደተኞችን ወደ ኢትዮጵያ መግባት ያረጋገጠ ሲሆን ከተመድ የስደተኞች ኮሚሽን፣ ከዓለም አቀፍ ፍልሰት ድርጅት፣ እንዲሁም ከኢትዮጵያ የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ጋር በመሆን የዳሰሳ ጥናት አካሂዷል።

ያንብቡ : telegra.ph/ER-02-22

@tikvahethiopia