#EHRC

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)፣ ከየካቲት 4 ቀን 2015 ዓ.ም. ምሽት ጀምሮ በተለያዩ የአዲስ አበባ እና የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች የተፈጸሙ እስሮችን በተመለከተ ፦

- የአዲስ አበባን፣ የፌዴራል እና የኦሮሚያ ክልል ፖሊስና የጸጥታ አካላት፣
- ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጽሕፈት ቤትን፣
- ምስክሮችን
- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን በማነጋገር እንዲሁም በአዲስ አበባ የተለያዩ ማቆያ ቦታዎችን በመጎብኘት ክትትል በማድረግ ላይ እንደሚገኝ አሳውቋል።

የተወሰኑ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች በፍርድ ቤት ወይም በፖሊስ ጣቢያ ዋስትና እየተለቀቁ መሆናቸውን ኮሚሽኑ ያረጋገጠ ቢሆንም አሁንም ብዙ ሰዎች ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ " በተለያየ ዓይነት ወንጀል ተጠርጥረዋል " በሚል ዋስትናም ተከልክለው በእስር ላይ ይገኛሉ ተብሏል።

ከተፈጠረው ሁኔታ ጋር ተያይዞ የዚህ ዓይነቱ እስር የዘፈቀደ እስር ሊሆን ስለሚችል የመንግሥት የወንጀል ፍትሕ አስተዳደር አካላት በሙሉ በበቂ ምክንያት በወንጀል የተጠረጠረን ሰው በሕጉ መሠረት ሰብአዊ መብቶችን ያከበረ በተለይም በቅድመ ምርመራ ወቅት የዋስትና መብት አጠባበቅ ሥርዓትን ባከበረ መንገድ ምርመራ ከማድረግ ውጪ ተገቢ ያልሆነ እስር እንዲያስወግዱ የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ አሳስበዋል፡፡

@tikvahethiopia