TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE የዩኒቨርሲቲዎች ምደባ ከዛሬ እኩለ ሌሊት ጀምሮ ይፋ ይደረጋል። በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ እና በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በወጪ መጋራት ትምህርታቸውን ለመከታተል ላመለከታችሁ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ዛሬ የካቲት 05/2015 ዓ.ም እኩለ ሌሊት ይፋ ይደረጋል። የተመደባችሁበትን ተቋም ለማወቅ ተከታዮቹን…
#MoE

ትላንት ለሊት ጀምሮ በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና 50 በመቶና በላይ ያመጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባቸውን እየተመለከቱ ይገኛሉ።

ተማሪዎች የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በተከታዮቹ አማራጮች ማየት ይችላሉ፦
Website:  https://result.ethernet.edu.et
SMS: 9444
Telegram bot: @moestudentbot

ከዚሁ ከዩኒቨርሲቲ ምደባ ጋር በተያያዘ ጥያቄ ያላቸው ተማሪዎች result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት Complaint የሚለውን በመጫን ጥያቄዎቻቸውን ማቅረብ እንደሚችሉ የትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

የትምህርት ሚኒስቴር ምንም አይነት ጥያቄም ሆነ ማመልከቻ #በአካል የማይቀበል መሆኑን ገልጿል።

በሌላ በኩል ፤ የሬሚዲያል ፕሮግራም መቁረጫ ነጥብ ዛሬ የካቲት 6 ቀን 2015 ዓ/ም ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያላስመዘገቡና የተሻለ ውጤት ካላቸው ተማሪዎች መካከል 100 ሺህ የሚሆኑት ተማሪዎች በሬሚዲያል ፕሮግራም እንደሚካተቱ መገለጹ ይታወቃል።

የሬሚዲያል ፕሮግራሙን ለአራት ወራት ከየካቲት 15 እስከ ሰኔ 15/2015 ዓ.ም ለመስጠት ታቅዷል።

More : @tikvahuniversity

@tikvahethiopia