#Update

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ክስ በመመስረት ሂደት ላይ መሆኗን አሳወቀች።

ቤተክርስቲያኗ ይህን ያሳወቀችው ዛሬ ከህግ ባለሙያዎች ጋር በመሆን በሰጠችው መግለጫ ነው።

ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ለመመስረት ጥያቄ የቀርበ ሲሆን ክስ የመመስረት ሂደት ጊዜ ስለሚፈልግ ጊዜያዊ እግድ እንዲሰጥ ጥያቄ መቅርቡ ታውቋል።

ክሱ / እግዱ የቀረበው በልደታ ምድብ ሁለተኛ መሰረታዊ መብቶች እና ነፃነቶች ምድብ ችሎት ላይ መሆኑ ተገልጿል።

ክስ የቀረበባቸው ተጠሪዎች በቀድሞ ስማቸው 1ኛ. አባ ሳዊሮስ ፣ 2ኛ. አባ ኤዎስጣቴዎስ ፣ 3ኛ. አባ ዜና ማርቆስ ፤ እንዲሁም ኤጲስቆጶሳት ተብለው ተሹመዋል ተብሎ መግለጫ የተሰጠባቸው 25 ግለሰቦች ያሉበት መሆኑን ቤተክርስቲያኗ ገልጻለች።

አንድ ግለሰብ ተፀፅተው ስለተመለሱ ክሱ እንደማያካትታቸው ቤተክርስቲያን ጠቁማለች።

በተጨማሪ ፤ ጠበቃ ኃይለሚካኤል ከፈሌ ተጠሪ ሆነው የተካተቱ መሆኑ ተገልጿል።

ሌሎች ፦
- የፌዴራል ፖሊስ
- የኦሮሚያ ክልል መንግስት
- የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ የክሱ / የአቤቱታው አካል መሆናቸውን ቤተክርስቲያን አሳውቃለች።

ክስ የቀረበው ለምንድነው ? ቤተክርስቲያኗ ክስ ያቀረበችው ህጋዊ ሰውነቷን የጣሰ ህገወጥ ድርጊት ስለተፈፀመ፣ በአገልጋዮች አባቶች ፣ ካህናት እና ምዕመናን ላይ በደል ስለተፈፀመ መሆኑ ገልጻለች።

ቤተክርስቲያኗ ህገወጥ ብላ በይፋ የፈረጀችው ቡድን ወደ ቤተክርስቲያን ቅጥር እንዳይደርስ፣ ንብረት እንዳያንቀሳቅስ፣ የቤተክርስቲያኗ ጥቅምና መብት እንዲከበር ይህ ክስ በዝርዝር እስኪታይ የዕግድ ትዕዛዝ እንዲተላለፍ ለፍርድ ቤት ጠይቃለች።

ተጨማሪ መረጃዎች ይኖራሉ።

@tikvahethiopia