#Afar

የዲጂታል ቴክኖሎጂን ለሰላምና ግንባታ የመጠቀም ልምድ ደካማ በሆነበት ሁኔታ በማኅበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ ሀሰተኛና የጥላቻ ንግግሮች ጉዳታቸው ትልቅ ነው።

በተለይ እነዚህ አደገኛ መረጃዎች በከተማም ሆነ ከተማ ወጣ ባሉ አከባቢዎች የሚፈጥሩት ተጽዕኖ ከፍ ያለ ነው።

ይህንን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ከጥር 13 ጀምሮ ለ4 ቀናት በዲጂታል ሰላም ግንባታ እንዲሁም መሰረታዊ የሚዲያ ክህሎት ላይ ትኩረቱን መሰረት ያደረገው የአሰልጣኞች ስልጠና (TOT) በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ተካሂዷል።

በስልጠናው 20 ወጣቶች ተሳታፊ የነበሩ ሲሆን ከክልሉ 4 ወረዳዎች (አሚባራ፣ አፋንቦ፣ ጭፍራ፣ ገዋኔ) ለተወጣጡ ሰልጣኞች የዲጂታል ሚዲያ ክህሎትን ስለማሳደግ፣ የሰላም ግንባታ ሥራዎችን ስለመስራትና ከሀሰተኛና ጥላቻ ንግግሮችን ራስንና ማኅበረሰብን ስለመከላከል በዚህም ምክንያት የሚደርስን ጉዳት መቀነስ በሚቻልበት አግባብ የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጥቷል።

በቀጣይም ወጣቶቹ በወሰዱት ሥልጠና መሰረት ወደ ማኅበረሰባቸው ተመልሰው ለሌሎች እኩዮቻቸው ተመሳሳይ ሥልጠናዎችን እንዲሰጡ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ በአከባቢያቸው አወንታዊ ተጽዕኖ እንዲፈጥሩ ለማስቻል ታቅዷል።

በተለይ የመረጃ ተደራሽነቱ በተለያዩ ምክንያቶች ለተገደበባቸው አከባቢዎች መሰል የአቻ ሥልጠናዎች ትርጉም ያለው ለውጥ ከማምጣቱም በዘለለ ወጣቱን አሳታፊ ያደረገ የመፍትሔ ሀሳቦች ተግባራዊ እንዲሆኑ እድሉን በሰፊው ያመቻቻል።

ይህንን ስልጠና ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከ Mercy Corps Ethiopia ጋር በጋራ በመሆን ለሥልጠናው ከሚያስፈልገው የሥርዓተ ትምህርት ቀረጻ ጀምሮ በጋራ እየሰሩ ይገኛሉ።

በቀጣይ በድሬደዋና በጅጅጋ ከተሞች መሰል ሥልጠናዎችን የሚሰጡ ይሆናል።

@tikvahethiopia