TIKVAH-ETHIOPIA
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ወደ ኢትዮጵያ (አዲስ አበባ) እንደሚመጡ ተሰምቷል። የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኪን ጋንግ በቅርቡ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙ ሲሆን ወደ አዲስ አበባ የሚመጡት በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ እንደሆነ ተሰምቷል። ኪንግ ጋንግ የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ከመሾማቸው በፊት በአሜሪካ የቻይና አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል።…
#ETHIOPIA #CHINA

የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋንግ ኢትዮጵያ ይገኛሉ።

ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ይፋዊ የሆነ የሥራ ጉብኝት እያደረጉ እንደሚገኙ የተገለፀ ሲሆን ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ ከገቡ በኃላ ከኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እንዲሁም ከምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር ተገናኝተው መክረዋል።

ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከሚኒስትሩ ጋር ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ ባሰራጩት አጭር ፅሁፍ ፤ " የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት አሁንም ጸንቶ ቀጥሏል " ብለዋል። " የዛሬው ውይይት ይህንን እና በልማት የምንጋራውን ስልታዊ የጋራ ዓላማ፤ እንዲሁም አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ትብብርን አጉልቶ አሳይቷል " ሲሉ ገልፀዋል።

የቻይናው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከአቶ ደመቀ ጋር በተገናኙበት ወቅት የፖለቲካ ምክክር ማድረግ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት እና ከፊል የዕደ ስረዛ ስምምነት ተፈርሟል።

ስምምነቱ የሁለቱን አገራት ጠንካራ ግንኙነትን ለማስቀጠል እና ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋጋር እንደሚረዳ ተገልጿል።

የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በሁለትዮሽ ፣ቀጣናዊ እና በዓለም አቀፍ መድረኮች ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር መስራቷን አጠናክራ እንደምትቀጥል አሳውቀዋል።

ቺን ጋንግ በቅርቡ ወደ ስልጣን የመጡ ሲሆን የመጀመሪያ ጉብኝታቸውን በ #ኢትዮጵያ እያደረጉ ናቸው።

መረጃው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia