#US

አሜሪካ መላ ዜጎቿን ለመግደል በቂ የሆነ " ፌንታሊን " የተሰኘ አደንዛዥ ዕፅ ማያዟን አስታወቀች።

የአሜሪካ የዕጽ ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን እየተጠናቀቀ ባለው 2022 መላውን የአሜሪካ ዜጋ ለመግደል በቂ የሆነ " ፌንታሊን " የተሰኘ አደገኛ አደንዛዥ ዕጽ መያዙን አሳውቋል።

ባለስልጣኑ፤ በአንዴ እንዲወሰዱ ተደርገው የተዘጋጁ እያንዳንዳቸው ሁለት ሚሊግራም የሚመዝኑ ገዳይ የሆኑ 379 ሚሊዮን ፌንታሊን የተሰኘ ዕጾችን ይዣለሁ ብሏል።

ይህ አደንዛዥ ዕጽ ከሄሮይን 50 እጥፍ በላይ ገዳይ እንደሆነ የገለፀ ሲሆን "ፌንታኒል አሜሪካ በአሁኑ ወቅት የገጠማት ገዳይ ስጋት ነው " ሲል ገልጾታል።

ይኸው የዕፅ ተቆጣጣሪ መ/ቤት እንደሚለው፤ ከፍተኛ መጠን ያለው ፌንታሊን ወደ አሜሪካ የሚገባው #ከሜክሲኮ ሲሆን ከ4 ሺ 500 ኪግ በላይ ፌንታሊንና 50.6 ሚሊዮን በእንክብል መልክ የተዘጋጁ ዕጾች ተይዘዋል።

በእንክብል መልክ የተዘጋጁት ዕጾች ህመም ማስታገሻ መድኃኒቶች እንዲመስሉ መደረጋቸውን ተገልጿል።

እየተጠናቀቀ ባለው በዚህ የፈረንጆቹ ዓመት የተያዘው የዕጽ መጠን ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በእጥፍ ጨምሯል።

አንደ ባለስልጣኑ መረጃ፤ በአሜሪካ የሚያዙት ዕጾች " በሲናሎዋ እና ጃሊስኮ " ዕጽ አዘዋዋሪ ቡድኖች አማካይነት ሜክሲኮ ውስጥ በምስጢራዊ ስፍራ በሚገኙ ፋብሪካዎች ይመረታሉ።

"ፌንታሊን" እጅግ አደገኛ የሆነ ዕጽ ሲሆን የእርሳስ ጫፍ ላይ ልትቀመጥ የምትችል ትንሽ መጠን እንኳን የመግደል አቅም አላት።

ማጠቃለያ፦

- ባለፈው ዓመት 100 ሺ አሜሪካውያን ከመጠን በላይ ዕጽ ወስደው ሕይወታቸው አልፏል። ከዚህ ውስጥ ሁለት ሦስተኛው ሞት ከፌንታሊን ጋር የተገናኘ ነው።

- በዚህ ዓመት የተያዘው ፌንታሊን መጠን 330 ሚሊዮን የአሜሪካ ነዋሪዎች መግደል የሚችል ነው።

#BBC

@tikvahethiopia