" ... አሽከርካሪ እየተንገላታ ነው። እንደድሮው 24 ሰዓት ተንቀሳቅሶ ሥራ መሥራት አልቻለም " - አቶ ዳመነ ተሾመ

ከጥቅምት 10 ቀን 2015 ዓ. ም ጀምሮ እስካሁን ባለው አንድ ወር ጊዜ ውስጥ ከአዳማ እስከ መተሃራ ባለው አውራ ጎዳና የሚንቀሳቀሱ 5 የአገር አቋራጭ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ታግተው ተወስደው 3ቱ #በሕይወት_እንዳልተገኙ ተነግሯል።

የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማሕበር አመራር አባል አቶ ዳመነ ተሾመ ለዶቼ ቬለ ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል ፤ " ታግተው ጫካ ከተወሰዱት 5 ሹፌሮች መካከል ገንዘብ ከፍለው የወጡ አሉ " ብለዋል።

አቶ ዳመነ ፤ ይህንን እገታ የፈፀሙትን አካላት ማንነት እንዳላወቁትና መንግሥትም የደረሰበት እንደማይመስላቸው ተናግረዋል።

" በኮሪደሩ ላይ ከፍተኛ ችግር እየተፈጠረ ነው። አሽከርካሪ እየተንገላታ ነው። እንደድሮው 24 ሰዓት ተንቀሳቅሶ ሥራ መሥራት አልቻለም " ብለዋል።

ማሕበራቸው ከኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሰሪዎች ኤጀንሲ እና ከኢትዮጵያ ሠራተኞች ማሕበራት ኮንፌደሬሽን ጋር ትናንት በችግሩ እና መፍትሔዎች ዙሪያ መወያየቱን ገልፀው ፤ " የሾፌሮች መታገት እና መንገላታት ይቁም። እኛ የአበል፣ የደሞዝ ጥያቄ ሳይሆን መንግሥት #ከለላ እና #ጥበቃ ያድርግልን የሚለውን ሀሳብ አንሸራሽረናል " ሲሉ ተናግረዋል።

" በዋናነት ከአዳማ እስከ መተሃራ በምእራብ ወለጋ አካባቢ የሚንቀሳቀሱ አሽከርካሪዎች ችግር ውስጥ እንደሆኑ የጠቆሙት አቶ ዳመነ አሽከርካሪዎቻችን ወደ ቤታቸው ለመግባት በየመንገዱ ችግር እየተፈጠረባቸው ወደ 21 ቀናቶችን ፈጅቶባቸዋል " በማለት የሚገጥማቸው ችግር ምን ያህል አሳሳቢ እየሆነ እንደመጣ አስገንዝበዋል።

ምንጭ፦ ዶቼ ቨለ ሬድዮ

@tikvahethiopia