የICRC ተሽከርካሪዎች መቐለ ገብተዋል።

የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ፤ የሰብአዊ ድጋፍ የጫነ የመጀመሪያ ኮንቮይ ትግራይ ክልል መዲና መቐለ መግባቱን አሳውቋል።

ትግራይ ውስጥ የሚገኙ የጤና ተቋማትን ለደገፍ ፤ አስቸኳይ ህክምና የሚሹ ህሙማንን ለማከም መድሀኒት ፣ የድንገተኛ እና የመጀመሪያ እርዳታ መስጫ ቁሳቁሶችን የያዙ ሁለት ተሽከርካሪዎች ናቸው መቐለ የደረሱት።

የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቶ በሚቀጥሉት ቀናት ሌሎች ተጨማሪ ድጋፎች ይገባሉ ብሏል።

@tikvahethiopia