#Update

" ማንኛውም የሰብዓዊ ድጋፍ አቅራቢ ተቋም በአየር እና በየብስ የሰብዓዊ እርዳታ ማቅረብ ይችላል " - የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን

ዛሬ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ፤ ወደ ትግራይ ክልል የሚወስዱ #ሁሉም ኮሪደሮች ለሰብአዊ ደጋፍ አቅርቦት ክፍት መደረጋቸውን አስታውቋል።

የሰብአዊ ድጋፍ ተቋማት በአየርና በየብስ የሰብዓዊ እርዳታ ማቅረብ እንደሚችሉ ገልጿል።

ይህ የተገለፀው የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አምሳደር ሽፈራው ተክለማርያም ለተለያዩ #ዓለም_አቀፍ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅራቢ ድርጅቶች የሰሜን ኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታን በተመለከተ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው።

አምባሳደር ሽፈራው ፤ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የተደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ሰብአዊ ድጋፍ ለሚያቀርቡ ተቋማት የየብስም ሆነ የአየር ትራንስፖርት ክፍት ተደርጓል ሲሉ ገልጸዋል።

በአፋር ክልል ከአብዓላ መቐለ ፣ በሁመራ በኩል ሽራሮ ፣ ሽሬ አክሱም አድዋ፤ በጎንደር አዲ አርቃይ ማይጸምሪ ሽሬ እንዲሁም የወልዲያ አላማጣ መስመሮች ሁሉም ለሰብዓዊ እርዳታ ክፍት እንደሆኑ ተናግረዋል።

በአፋር ክልል ከአብዓላ መቐለ መስመር የሙከራ አገልግሎት የሰጠ ሲሆን፤ በሁመራ በኩል ሽራሮ፣ ሽሬ አክሱም አድዋ በኩል ከገቡ 16 ከባድ መኪናዎች መካከል 3ቱ የሕክምና ቁሳቁስ ይዘው መግባታቸውን አመልክተዋል።

" ማንኛውም የሰብዓዊ ድጋፍ አቅራቢ ተቋም በአየር እና በየብስ የሰብዓዊ እርዳታ ማቅረብ ይችላል " ብለዋል ኮሚሽነሩ።

#ENA

@tikvahethiopia