" የሰላም ስምምነቱን መደገፋችንን እንቀጥላለን " - አውሮፓ ህብረት
የአውሮፓ ህብረት የሰላም ስምምነቱን መደገፉን እንደሚቀጥል ዛሬ ባሰራጨው ፅሁፍ አረጋግጧል።
" ከሰላም ውጭ አማራጭ የለም " ያለው ህብረቱ አጋሮቹ UNICEF እና PLAN የህብረቱን የገንዘብ ድጋፍ በተግባር ላይ ማዋል ይጀምራሉ ሲል አመላክቷል።
የአውሮፓ ህብረት ፤ ለሕዝብ አፋጣኝ ቀጥተኛ ድጋፍ ለማረጋገጥ ሥራችንን እንቀጥላለን ብሏል። ህዝቡም የህብረቱን እንቅስቃሴ ይከታተል ዘንድ ጥሪ አቅርቧል።
ትላንት ህብረቱ የኢትዮጵያን ህዝብ #በቀጥታ እንደሚረዳ ገልጾ የትምህርት እና ጤና ዘርፉን ለመደገፍ 38 ሚሊዮን ዩሮ ( 2.1 ቢሊዮን ብር) ለግሷል።
" ልጆች ወደ ትምህርት ቤት ይመለሳሉ " ኢትዮጵያውያን የጤና አገልግሎት ያገኛሉ። " ያለው ህብረቱ የአውሮፓ ዜጎች ከፕላን ኢንተርናሽናል (PLAN) ኢትዮጵያ እና ዩኒሴፍ (UNICE) ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ኢትዮጵያውያንን ይረዳሉ ሲል አሳውቋል።
@tikvahethiopia