TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ለመጀመሪያ ጊዜ በፌዴራል ተቋማት / ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እየተሰጠ የሚገኘው የ2014 ዓ/ም 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የመጀመሪያው ዙር / የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ተጠናቋል። ከጥቅምት 5/2015 ዓ/ም ጀምሮ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች መግባት ይጀምራሉ። ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ፤ የተማሪዎች ጉዳይ የሀገር ጉዳይ ስለሆነ ባለፉት ዓመታት የ12ኛ ክፍል ፈተናዎችን ጉዳይ በንቃት…
#Telegram

በኢትዮጵያ #የቴሌግራም አገልግሎት እንዲገደብ ተደርጓል። አገልግሎቱ ከእኩለ ቀን አንስቶ ነው የተገደበው።

እስካሁን በጉዳዩ ላይ በሚመለከታቸው አካላት ማብራሪያ ባይሰጥም ከዚህ ቀደም እንደታየው የቴሌግራም መገደብ ነገ ከሚጀምረው "የተፈጥሮ ሳይንስ" የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ይታመናል።

ባለፈው ሳምንት የማህበራዊ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናቸውን በሚወስዱበት ቀናት/ወደ ክፍል ገብተው ፈተናቸውን በሚወስዱበት ሰዓት / ፈተናውን ጨርሰው እስኪወጡ ድረስ የቴሌግራም አገልግሎት እንዲገደብ ሲደረግ ነበር።

" በማህበራዊ ሳይንስ " የፈተና ወቅት ተማሪዎች ከፈተና ክፍል ሲወጡ ቴሌግራም ወደ አገልግሎት ሲመለስ የነበረ ሲሆን አሁኑ ላይ ግን ከፈተና አንድ ቀን ቀደም ብሎ አገልግሎቱ ተገድቧል።

የቴሌግራም አገልግሎት በኢትዮጵያ ባሉት ሁለቱም የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢዎች ኢትዮ ቴሌኮም እና ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እንደማይሰራ ማረጋገጥ ችለናል።

ምንም እንኳን " የቴሌግራም " አገልግሎት ቢገደብም ሌሎች እንደ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም፣ ትዊተር የመሳሰሉ መተግበሪያዎች ያለ ገደብ እየሰሩ ናቸው።

የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ወቅት ወደ መፈተኛ ማዕከላት (ዩኒቨርሲቲ) ተማሪዎች ይዘው እንዳይገቡ በጥብቅ የተከለከለውን ስልክ ይዘው የገቡ ተፈታኞች ፈተናው እየተሰጠ ከመፈተኛ ክፍል እና ፈተና ሲጠናቀቅ ከማደሪያቸው የፈተና ወረቀቶችን በቴሌግራም ግሩፖች እና ቻናሎች ላይ ሲያሰራጩ ነበር።

በዚህም አንዳንድ ሰዎች " የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተሰርቋል " የሚሉ መረጃዎችን ቢያሰራጩም ፈተናው መሰጠት ከጀመረበት ሰዓት በፊት ቀድሞ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ስለመሰራጨቱ የሚያሳይ ማስረጃዎች ማግኘት አልተቻለም።

@tikvahethiopia