TIKVAH-ETHIOPIA
#Harari #SafaricomEthiopia በሐረሪ ክልል ፤ የ " ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ " መለያ በተለጠፈባቸው ሁሉም መደብሮች እና ሱቆች ሲም ካርድ እና የአየር ሰዓት መግዛት ይቻላል ተብሏል። በተጨማሪ በአራተኛ እና በሥላሴ አካባቢ ባሉት ሁለት የሽያጭ ማዕከሎቹ የሲም ካርድ ሽያጭ ምዝገባ፣ የስልክ ቀፎዎች ግዢ እና ልዩ ልዩ የደንበኞች ድጋፍ ማግኘት እንደሚቻል ተገልጿል። ደንበኞች ለማንኛውም የደንበኞች…
#ADAMA #BAHIRDAR

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት መጠነ ሰፊ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራውን በባሕር ዳር እና በአዳማ ከተሞች ጀምሯል።

ይህ የደንበኞች ሙከራ ከድሬዳዋ፣ ሐረር እና ሐረማያ በመቀጠል የሳፋሪኮምን ኔትወርክ ለመሞከር ባሕር ዳርን እና አዳማን 4ኛ እና 5ኛ የኢትዮጵያ ከተሞች አድርጓቸዋል።

የሲም ካርድ ሽያጭ ምዝገባ፣ የአየር ሰዓት እና የስልክ ቀፎዎች ግዢ እንዲሁም የደንበኞች ድጋፍ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መለያ ከተለጠፈባቸው መደብሮች እና ሱቆች ማግኘት እንደሚቻል ተገልጿል።

📍ባህር ዳር

አራት የሳፋሪኮም መለያ የተለጠፈባቸው መደብሮች (ቀበሌ 14 - የተባበሩት ፊትለፊት፣ ቀበሌ 16 - ኖክ ፊትለፊት፣ ቀበሌ 11 - አባይ ማዶ፣ ቀበሌ 12 - ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበብ ካምፓስ ፊትለፊት) ደንበኞችን ለማገልገል ክፍት ናቸው።

📍አዳማ

ሁለት የሳፋሪኮም መለያ የተለጠፈባቸው መደብሮች (ፍራንኮ እና ፖስታ ቤት አካባቢ) ደንበኞችን ለማገልገል ክፍት ናቸው።

በባሕር ዳር እና አዳማ ከተማ አገልግሎት በሚጀምረው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሙከራ ኔትወርክ ደንበኞች ዳታ መጠቀም፣ ጥሪዎች እና የጽሁፍ መልዕክቶችን ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እና ከኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ጋር መለዋወጥ እንዲሁም የዓለም አቀፍ ጥሪዎችን ማድረግ ይችላሉ፡፡

የሳፋሪኮም የጥሪ ማእከል 700 ሲሆን የደንበኞች አገልግሎት ሰራተኞችን በዚሁ ማግኝት ይቻላል። በአማርኛ ፣ አፋን ኦሮሞ፣ ሱማልኛ ፣ ትግርኛ እና እንግሊዝኛ ቋንቋ ድጋፍ ማግኘት ይቻላል።

@tikvahethiopia