#WorldBank #Ethiopia

የዓለም ባንክ ግሩፕ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን አጋርነት አጠናክሮ ለማስቀጠል ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል።

የዓለም ባንክ ግሩፕ ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ ያለው ግጭት በእጅጉ እንደሚያስበው አመልክቷል።

በርካታ ግጭቶች እንዲሁም በታሪክ የታየው አስከፊ ድርቅና ሌሎች ሁኔታዎች ጋር ተዳምረው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ክፉኛ በመጎዳታቸው ሀገሪቱ ባለፉት አመታት ያስመዘገበችውን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እድገት አደጋ ላይ ጥሏል ሲል ገልጿል።

የዓለም ባንክ ግሩፕ የኢትዮጵያ ህዝብ የበለጠ የመቋቋም አቅምን ለመደገፍ እና በግጭት ሁኔታዎች ውስጥ ድጋፉን ለመቀጠል ካለው ስትራቴጂ ጋር በሚስማማ መልኩ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጥቅም ሲል ከኢትዮጵያ ጋር ያለው አጋርነት አጠናክሮ እንደሚያስቀጥል ቁርጠኝነቱን አረጋግጧል።

በዚህም መሰረት የዓለም ባንክ ቡድን ኢትዮጵያ በመላ ሀገሪቱ የዜጎቿን መሰረታዊ አገልግሎቶች ማለትም የትምህርት፣ የምግብ ዋስትና፣ የጤና፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ፣ የሴቶች አቅም በማጎልበት፣  የማህበራዊ እና የአካባቢ ጥበቃን ለማሟላት በምታደርገው ጥረት ድጋፉን እያደረገ መሆኑን አሳውቋል።

የዓለም ባንክ ግሩፕ ልማት ላይ ያተኮረ ድርጅት እንደመሆኑ መጠን በአባል ሀገራቱ የውስጥ አስተዳደር ጉዳዮች ላይ የመሳተፍ ሥልጣን ባይኖረውም የልማት ተራድኦ ቡድን አባል እንደመሆኑ መጠን ደግሞ የሁሉንም ኢትዮጵያውያን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መወያየቱን እንደሚቀጥል ባወጣው መግለጫ ገልጿል።

(ተጨማሪ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia