TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #ደቡብ_ወሎ በደቡብ ወሎ ከታች ቀበሌ እስከ ዞን ድረስ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን ህዝቡን እንዲረጋጋ የማድረግ ስራ እየተሰራ ነው ተብሏል። በዞኑ ባሉ ወረዳዎች ውስጥ የሀገር መከላከያን ልብስ በመልበስ መከላከያ በመምሰል በአቋራጭ መንገዶች ሲጓዙ የነበሩ አካላት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል። በአሉባልታ ከሰሜን ወሎ ዞን የተፈናቀሉ በርካታ ሰዎች ወደ ዞኑ እየገቡ መሆኑን የገለፀው…
#Update

#ሰቆጣ

መላው የሰቆጣ ነዋሪዎች በአሉባልት እና ሀሰተኛ መረጃዎችን ሳይደናገሩ አካባቢያቸውን በንቃት እንዲጠብቁ ጥሪ ቀርቧል።

#ኮምቦልቻ

ዛሬ በኮምቦልቻ ከከተማው የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ በከተማው ከሚታወቁ ታዋቂ ግለሰቦች ጋር ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውይይት ተደርጎ ነበር።

በዚህም መድረክ ፤ የተለያዩ ሀሰተኛ አሉባልታዎች በመንዛት ህዝቡን ለማሸበር የሚደረጉ ጥረቶች መኖራቸው ተገልጾ መላው ነዋሪ ተረጋግቶ በንቃት አካባቢውን በመጠበቅ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በጋራ ሊሰራ ይገባል ተብሏል።

በሌላ በኩል ፤ በከተማዋ እስከሁን ባለው ከ400 በላይ ባጃጆች እና 80 ሞተሮች በህግ ቁጥጥር ስር ገብተው ማጣራት ተደርጎ ወደየመጡበት እንዲመለሱ መደረጉ ተገልጿል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች ሁሉም ነዋሪ በቀበሌና ቀጠና ብሎክ ተደራጅቶ አካባቢውን መጠበቅ እንዳለበትና በእቃ ዋጋ ላይ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ ጠበቅ ያለ ቁጥጥር ይደረግ ሲሉ ጠይቀዋል።

#ደሴ

ዛሬ በደሴ ከአምስቱም ክ/ከተሞች ከተውጣጡ ወጣቶች ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ውይይት ተደርጎ የነበረ ሲሆን በዚሁ መድረክ ሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳዎችን በማሰራጨት ህዝቡ ላይ የስነልቦና ጫና ለማሳደር ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

በዚህም የከተማው ወጣት በሙሉ በሀሰተኛ ወሬ እና በሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳ ሳይረበሽ ከመላው የከተማው ነዋሪ ጋር በመሆን አካባቢውን እና የከተማውን ሰላም ሊያረጋግጥ ይገባል ተብሏል።

በከተማው የፀጥታ ኮማንድ ፖስት መቋቋሙ ተነግሯል።

#ወልድያ

ወልዲያ ከተማ አዳሯ ሰላም የነበረ ሲሆን የዛሬ ውሎዋም ሰላም ነው። አሁንም ቢሆን መላው ነዋሪ ተረጋግቶ አካባቢውን በመጠብቅ የከተማዋን ሰላም ሊያረጋግጥ ይገባል ተብሏል።

@tikvahethiopia