#Gambella

በጎርፍ አደጋ ወገኖቻችን ተፈናቀሉ።

በጋምቤላ ክልል በ4 ወረዳዎች በደረሰ የጎርፍ አደጋ ከአራት ሺህ በላይ አባዎራና እማዎራ ወገኖቻችን ከመኖሪያ ቀያቸዉ ተፈናቅለዋል።

ከክልሉ አደጋ ስጋት አመራር በተገኘው መረጃ በሃገራችን ደጋማዉ አካባቢ በጣለዉ ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት በላሬ፣ በመኮይ በዋንቱዋና በኢታንግ ልዩ ወረዳ በሚገኙ ቀበሌዎች ላይ የጎርፍ መጥለቅለቅ ተከስቷታ።

የጎርፍ መጥለቅለቅ ከደረሰባቸዉ 4 ወረዳዎች ዉስጥ አራት ሺህ አንድ መቶ ሰላሳ ዘጠኝ አባዎራና እማዎራ ከመኖሪያ ቀያቸዉ የተፈናቀሉ ሲሆን ለጊዜዉ ደረቃማ በሆኑ አካባቢዎች እንዲሰፍሩ ተደርጓል።

የደረሰው ጉዳት ዝርዝር ፦
- በኢታንግ ልዩ ወረዳ 2040 አባወራና እማወራ፣
- በላሬ ወረዳ 1000፣
- በዋንቱዋ ወረዳ 619፣
- በመኮይ 480 አባወራና እማወራ የተፈቀሉ ሲሆን በጂካዎ ወረዳም ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።

የጎርፍ አደጋዉ በቤት ዉስጥ ያሉ ቁሳቁሶች እንዲሁም በቁም እንስሳት ላይ ጉዳት አድርሷሳ።

በጎርፍ አደጋ ከቤት ንብረታቸዉ ለተፈናቀሉ ነዋሪዎች የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የተገለፀ ሲሆን ከክልሉ መንግስትና ከሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት በመነጋገር አፋጣኝ ድጋፍ የሚደርስበት ሁኔታ ይመቻቻል ሲል የክልሉ አደጋ ስጋት አመራር አስታውቋል።

መረጃው ከክልሉ ኮሚኒኬሽን የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia