#GujiZone

• " እስከ ሃምሌ 15 ቀን 2014 ባለው ጊዜ የ12 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ ቁጥሩ ግን ሊጨምር ይችላል " - የሰባ ቦሩ ቡሳ ጎኖፋ ቢሮ

• " የሞቱት ዜጎች ምናልባት በፀጥታ ችግር ምክንያት ሊሆን ይችላል " - የጉጂ ዞን ኮሚኒኬሽን

በኦሮሚያ ክልል፣ በጉጂ ዞን ፤ ሰባ ቦሩ ወረዳ በድርቅ ምክንያት የወገኖቻችን ህይወት እያለፈ መሆኑ ተገለፀ።

በኦሮሚያ ክልል፣ በጉጂ ዞን በሰባ ቦሩ ወረዳ ረሃብ ተከስቶ 12 ሰዎች መሞታቸውን የወረዳው ቡሳ ጎኖፋ ቢሮ ማስታወቁን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

ቢሮው፤ እስከ ሃምሌ 15 ቀን 2014 ዓ/ም ባለው ጊዜ ብቻ የ12 ሰዎች ህይወት ማለፉን ገልጾ ቁጥሩ ግን ሊጨምር እንደሚችል አሳውቋል።

በወረዳው 35,442 ዜጎች አስቸኳይ ምግብ እርዳት ያስፈልጋቸዋል የተባለ ሲሆን እነዚህ ዜጎች በንሳ ፣ በደጋላልቻ ፣ ሰባሎሌማሞ ፣ በኡቱሉ፣ ኦዴ ፣ ሀራጌሳ ቀበሌዎች ያሉ ናቸው ተብሏል።

የወረዳው ቡሳ ጎኖፋ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት መኮና ሀጤሳ ፤ ለወረዳው አልፎ አልፎ የምግብ እርዳታ ቢመጣም ምግብ ከሚያስፈልጋቸው ዜጎች ጋር የሚመጣጠን አይደለም ብለዋል።

በወረዳው የሟቾች ቁጥር በየቀኑ #እየጨመረ ሲሆን ባለፉት 2 ወራት የምግብ እና መሰል እርዳታቸዎች መቋረጣቸው ማህበረሰሙ ለከፋ የምግብ እጥረት መጋለጡን ገልፀዋል።

የጉጂ ዞን የኮሚኒኬሽን ቢሮ በበኩሉ ፤ በዞኑ ቆላማ አካባቢዎች 5 ወረዳዎች ድርቅ ተከስቷል ብሏል።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ኦልኮ፤ " በረሃብ ምክንያት ስለሞቱ ሰዎች መረጃ የለኝም " ብለዋል። ነገር ግን " በአካባቢው የፀጥታ ችግር አለ " ሲሉ መግለፃቸውን ሪፖርተር ዘግቧል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Guji-Zone-08-04

@tikvahethiopia