#DrAbiyAhmed

ዛሬ ከሰዓት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ አባላት ስብሰባ የተካሄደ ሲሆን በአጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ መክሯል።

እንዲሁም የአረንጓዴ ዐሻራ ክንውን ያለበትን ደረጃ አንስቷል።

በተጨማሪም የ2015 የበጀት ዓመት ዕቅድ የትኩረት አቅጣጫን መቃኘቱን የጠ/ሚ ፅ/ቤት አሳውቋል።

ዶ/ር ዐቢይ ስብሰባውን በተመለከተ ፤" ባለፈው ዓመት የሚያበረታታ የወጪ ንግድ አፈጻጸም፣ ቀጥተኛ የውጭ ሙዓለ ነዋይ ፍሰት መጨመር ታይቷል። ባለፉት ሁለት ወራት የዋጋ ግሽበት መቀነስ፣ ከፍተኛ የአረንጓዴ ዐሻራ ክንውን፣ የበጎ ፈቃደኝነት ተግባራት፣ የሬሚታንስ ጭማሪ እና በቴክኖሎጂ የታገዘ የሥራ ክንውን የተመዘገቡበት እንደ ሆነ አረጋግጠናል። በዚህ ዓመት የተገኙ ስኬቶችን አጠናክሮ መቀጠል በእጅጉ አስፈላጊ ነው። " ብለዋል።

@tikvahethiopia