#ትኩረት📣

ነዋሪዎችን ከፍተኛ ስጋት ላይ የጣለው የፀጥታ ችግር !

ከቲክቫህ ቤተሰብ አባል ከአጣዬ አካባቢ ፦

" እንደ ሁል ጊዜው ሁሉ አጣዬ ከተማ ዳግም ከፍተኛ የፀጥታ ስጋት ውስጥ ገብታለች።

ይሄም የሆነው በሰሜን ሸዋ እና በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር አዋሳኝ ቦታዎች ዳግም ግጭት በመቀስቀሱ ነው።

ትላንት ማለትም በ02/11/2014 " የቤት እንሰሶች የተዘራ ሰብልን በሉብን " በማለት ልዩ ቦታው አርሶ አምባ የሚባል ስፍራ ፀብ የተነሳ ሲሆን አሁን ላይ አድማሱ ሰፍቶ በተለያየ አቅጣጫ ከባባድ ውጊያዎች ተከፍተዋል።

የተለያዩ የፀጥታ አካላትም ጉዳት ደርሶባቸው በአጣዬ ሆስፒታል ሲገቡም ተመልክተናል።

ቦታዎቹ ላይ ልዩ ሀይል እና ፌደራል ፖሊስ ያለ ቢሆንም እጅግ ብዙ ቁጥር ያለው ሀይል ነው ጥቃቱን እየሰነዘረ የሚገኘው።

ስለሆነም ለማብረድ እንደተቸገሩ እየተሰማ ነው የሚገኘው።

ከከሰአት ጀምሮ ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ የሚወስደው መንገድም እንደተዘጋ እና ከወትሮው በተለየ መልኩ የመኪኖች እንቅስቃሴ ቀንሷል።

የፌደራል መንግሥቱ እና የሚመለከታቸው አካላት ይሄንን ነገር አሁን ካለበት ሳይባባስ ትኩረት ሊሰጡት ይገባል። "

በአካባቢው ግጭት መቀስቀሡን የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ታደሰ ገብረፃዲቅ ለአል አይን ኒውስ ያረጋገጡ ሲሆን ግጭቱ ሳይባባስ ለማስቆም ተጨማሪ ሀይል ወደ ስፍራው ተልኳል ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

@tikvahethiopia