የነዳጅ ድጎማ !

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በአዲሱ የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ሥርአት ተጠቃሚ የማይሆኑ ተቋማትና ተሽከርካሪዎች በ4 ወራት ጊዜ ውስጥ ከመንግሥት የሚያገኙት የነዳጅ ድጎማ ሙሉ ለሙሉ ተነስቶ ዋጋውን ራሳቸው እንደሚሸፍኑ አስታውቋል።

ለ3 ወራት ግን መንግስት ከሚገዙት ነዳጅ ውስጥ ከ25 እስከ 75 በመቶ ዋጋ እንደሚደጉም ዛሬ በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተነግሯል።

በሌላ በኩል ፤ ድጎማ የሚደረግላቸው የሕዝብ ትራንስፖርት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ድጎማ ደግሞ በቀጣይ 5 ዓመታት ውስጥ እንደሚነሳ ተገልጿል።

በዚህም መንግሥት በየስድስት ወሩ ተፈፃሚ በሚያደርገው ሥርዓት መሰረት 10 በመቶ ድጎማን እያነሳ የሚሄድ ሲሆን በቀጣይ 5 ዓመታት ውስጥ በድጎማ የሚደገፋ የሕዝብ ትራንስፖርት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ከድጎማ የሚወጡ ይሆናል ተብሏል።

መረጃው የኢትዮ ንግድ እና ኢንቨስትመንት መድረክ እና WMCC ነው።

@tikvahethiopia