#DireDawaUniversity

በትግራይ ክልል ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በጊዚያዊነት ተመድበው ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ነባር ተማሪዎች " ግቢው ውጡ አለን " ሲሉ ቅሬታቸውን አድርሰውናል።

ተማሪዎቹ "ግቢውን ለቀን እንድንወጣ ተነግሮናል"፣ "የምግብ አገልግሎትም ተቋርጦብናል" ሲሉ ቅሬታቸውን ያቀርባሉ።

በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸው የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት መገርሳ ቃሲም (ዶ/ር) ተከታዩን ምላሽ ሰጠውናል።

"መደበኛ ነባር ተማሪዎች በግቢው መቆየት የሚችሉት እስከ ሰኔ 30/2014 ዓ.ም ብቻ ነው። ከሰኔ 30 በኋላ ዩኒቨርሲቲው የክረምት ተማሪዎችን ይቀበላል። በመሆኑም መደበኛ ነባር ተማሪዎችን የምናቆይበት አሰራር የለም።"

"በኮቪድ-19 ምክንያት የተደራረቡና የምንቀበላቸው 5 ሺህ የሚሆኑ የክረምት ተማሪዎች አሉብን። በቅርቡ የተቀበልናቸው የመጀመሪያ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች በግቢው ውስጥ ነው የሚገኙት። ከዚህ በተጨማሪ ከፍተኛ የበጀት እጥረት ገጥሞናል።"

በመሆኑም ሁሉም መደበኛ ነባር ተማሪዎች ግቢውን ለቀው እንዲወጡ መወሰኑን ምክትል ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።

ተቋሙ በአካዳሚክ ካላንደሩ መሰረት ነው የሚሰራው ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንቱ፤ ተማሪዎቹ የዩኒቨርሲቲውን ውሳኔ ሊያከብሩ ይገባል ብለዋል።

More : @tikvahuniversity