TIKVAH-ETHIOPIA
" ያለበት እስካሁን አልታወቀም " የገጣሚ በላይ በቀለ ወያ ቤተሰቦች ልጃቸው አሁንም የት እንዳለ ማወቅ እንዳልቻሉ ገልፀዋል። በልጃቸው አድራሻ አለመታወቅ ሳቢያ ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ የወደቁት ቤተሰቦች ልጃቸውን የወሰደ አካል በሰላም እንዲመልስ እየጠየቁ ይገኛሉ። " ጥፋት ካለበት አይጠየቅ እያልን አይደለም " ያሉት ቤተሰቦቹ መንግስት አስሮትም ከሆነ አድራሻውን እንዲያሳውቃቸው ህግን ባከበረ መልኩ…
#Update

ለቀናት ያህል የት እንደነበር ያልታወቀው ገጣሚ በላይ በቀለ ወያ ትላንት ምሽት ወደቤቱ መመለሱ ታውቋል።

ገጣሚ በተረጋገጠው የማህበራዊ ትስስር ገፁ ፤ " ከልዑል እግዚአብሔር ቀጥሎ ላዘናችሁልኝ ፣ ለራራችሁልኝ ፣ ለተጨነቃችሁልኝ ፣ ድምፅ ለሆናችሁኝ ሁሉ ከልቤ አመሠግናለሁ ። በህይወት ወደ ቤቴ ተመልሻለሁ ። ደህና ነኝ " ኢትዮጵያ ለዘልዓለም ትኑር " ሲል ፅፏል።

ገጣሚው በማን ፣ እንዴት እንደተወሰደ እንዲሁም የት እንዳነበረ በዝርዝር አልፃፈም።

ባለፉት 7 ቀናት ያለበት ባለመታወቁ እናት እና አባቱ አጠቃላ ቤተሰቦቹ ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ወድቀው እንደነበር እና መንግስትም ሆነ ሌላ አካላ ልጃቸውን በሰላም እንዲመልስላቸው ጥሪ ሲያቀርቡ እንደነበር ይታወሳል።

@tikvahethiopia