TIKVAH-ETHIOPIA
" ከሟቾች መካከል ሴቶች እና ህፃናት ይገኙበታል " - የቲክቫህ አባል ዛሬ በቄለም ወለጋ ለምለም ቀበሌ በተፈፀመ ጥቃት በርካታ ሰዎች ተጨፍጭፈዋል። እሱና ቤተሰቦቹ በአካባቢው ነዋሪ የሆኑ የቲክቫህ አባል ዛሬ የተፈፀመው ጭፍጨፋ እጅግ በጣም አሳዛኝ እንደነበር ገልፆ በርካታ ሰው ተገድላል፤ ሴቶች እና ህፃናትም ይገኙበታል ብሏል። በአካባቢው ኔትዎርክ ይሰራ ነበር አሁን ላይ እየሰራ አይደለም ቤተሰቦቼ…
የቄለም ወለጋው ጥቃት ...

" ... ጥቃት አድራሾቹ እጅግ በጣም የታጠቁ እና የተደራጁ ናቸው።

እዛ ያለው ማህበረሰብ ምስኪን ገበሬ ነው የዕለት ጉርሱን ዳፋ ቀና ብሎ የሚያገኝ ነው።

መብራት እንኳን በቅጡ የሌለው አካባቢ ነው። ከቦቀሎ እና ማሽላ እንጀራ በዘለለ የማይበላ ፤ በኑሮው የተጎሳቆለ ማህበረሰብ ነው እንኳን ጥይት እና ገጀራ ሊገባው ! እጅግ ምስኪን ማህበረሰብ ነው ።

ሰው ወዳድ ናቸው ፤ እንግዳም ተቀባይ ናቸው ፤ ያላቸውን አውጥተው የሚያስተናግዱ ናቸው። ፍርድ ከላይ ነው ፤ ፍርድ ከአላህ ነው ለዛ ማህበረሰብ ይሄ አይገባውም ነበር።

በሚያሳዝን ሁኔታን የማህበረሰቡን ሮሮ፣ ጩኸት ማን እንደሚሰማው አናውቅም። ጥቃት አድራሾቹን ማን ሃይ እንደሚላቸውም አናቅም።

ለማን አቤት እንደምንል ግራ የሚገባ ነው። ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ነው ባለፈው ከፍ ብሎ ጊምቢ አካባቢ በጣም ብዙ ሰው በተሰመሳሳይ ሁኔታ ተጨፍጭፏል።

ዘር እየተመረጠ ሰው የሚጨፈጨፍበት ጊዜ ላይ ደረስን ፤ ለማን አቤት እንደምንል አናውቅም " - በአከባቢው ቤተሰቦቹ ያሉ የቲክቫህ አባል ከተናገርው በጥቂቱ

ከላይ ያለው መልዕክት እየተላኩት ካሉ በርካታ መልዕክቶች አንዱ ነው። ቤተሰቦቻቸው እዛ ያሉ የቲክቫህ አባላት መልዕክት እየላኩ ነው።

ዛሬ ጭፍጨፋ በተፈፀመበት አካባቢ አስክሬን የመሰብሰብ ስራ እየተሰራ ሲሆን ፤ መከላከያውም በቦታው አለ ተብሏል።

እጅግ በርካታ ሰዎች ፤ ምንም ማያውቁ ምስኪን ህፃናት እና ሴቶችን ጨምሮ የተጨፈጨፉት። በርካቶች ህይወታቸውን ለማትረፍ ወደ መቻራ መሄዳቸውን ለማውቅም ተችሏል።

አሁንም አጠቃላይ ቀጠናውን ደህንነት ማረጋገጥ ካልተቻለ ሌላ ጥቃት ይፈፀማል የሚል ስጋት አይሏል።

(ውድ ቤተሰቦቻችን መልዕክቶችን አደራጅተን እንደጨረስን እንልካለን)

@tikvahethiopia