TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ጥንቃቄ

" FIAS 777 " የተባለ ሰዎችን ትርፋማ አደርጋለው በሚል ከበርካቶች ኤጀንት በሚላቸው አካላት በኩል ገንዘብ ሲሰበስብ ከርሞ ዛሬ አድራሻውን ጥፍትፍት አድርጓል።

#ሌሎችም፦ መሰል ስራ የሚሰሩ አሉ፤ መደረግ ስላለበት ጥንቃቄ ከዚህ በፊት ያሰራጨነውን በድጋሚ ለማቅረብ ወደድን ፦

#REPOST

" የተለያዩ ገንዘብ የማግኛ ማትረፊያ መንገዶች " እየተባለ በዲጅታል ሚዲያው በኩል ከቀርብ ጊዜ ወዲህ በርካቶች እጅግ በስፋት እየተከሰቱ ነው።

እነዚህ አካላት ፍቃድ ይኑራቸው አይኑራቸው ፤ የመስሪያ አድራሻቸው ይታወቅ አይታወቅ ፣ የሚመራቸው / የሚያስተባብራቸው ግለሰብ ይኑር አይኑር የሚለውን በግልፅ ለማወቅ አዳጋች ነው።

ውድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ከዚህ በፊትም እንዳልናችሁ ገንዘብ ሊያስገኝ የሚችል እንቅስቃሴ ውስጥ ስትገቡ / ኢንቨስት ስታደርጉ እነዚህ ጥያቄዎች እንድትጠይቁ አደራ እንላለን ፦

1. ድርጅቱ / ተቋሙ እውቅና ያለው ፣ ፍቃድ ያለው ነው ? የሚሰራበትን ፍቃድ በይፋ አሳውቋል ?

2. በትክክል የሚታወቅ አድራሻቸው የት ነው ? ቢሯቸው ?

3. ለሚደርስብኝ ማንኛውም አይነት ነገር ማንን ተጠያቂ ማድረግ እችላለው ?

4. የሚሰራው ስራ ምን ያህል ቀጣይነት አለው ? ነገ እንደማይቆም ምን ማስተማመኛ አለ ? ይህንን ማንስተማመኛ ማን ይሰጠኛል ? የሚሉ ጥያቄዎችን መጠየቅ ያስፈልጋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማህበራዊ ሚዲያው ላይ የማጭበርበር እና የማታለል ድርጊቶች እየሰፉ በመሆናቸው ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል።

ብዙሃንን ሊጠቅም ያሚችል ማንኛውም ህጋዊ ስራ በሚስጥር፣ በድብቅ ፈፅሞ ሊሰራ አይችልም እና ውድ ቤተሰቦቻችን ማንኛውም እንቅስቃሴ ስትጀምሩ ከላይ የተዘረዘሩ ጥያቄዎችን በቅድሚያ መልስ እንዳያገኙ አድርጉ።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia