#WorldBank

የምሥራቅ አፍሪካ አገራት በአስርት ዓመታት ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ከፍተኛ የኑሮ ውድነት እንደተጋረጠባቸው የዓለም ባንክ ከሰሞኑ አስታውቋል።

የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት እንዲሁም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጫና ተደማምሮ አንዳንድ አገራት ከፍተኛ የኢኮኖሚ ድቀት እያጋጠማቸው መሆኑን ባንኩ ገልጿል።

ከዚህም ጋር ተያይዞ ዓመታዊ ትንበያውን ቀንሷል።

ባንኩ በተለይም የምሥራቅ አፍሪካ አገራት እና አንዳንድ የአውሮፓ ክፍሎች ተጎጂ ሆነዋል ብሏል።

ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት እና ዝቅተኛ የምጣኔ ሀብረት ዕድገት ጥምረት ከ1970ዎቹ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊመለስ እንደሚችልም ጠቁሟል።

አገራቱ በምግብ እና በነዳጅ ዋጋ መጨመር ምክንያት ቀውስ እያጋጠማቸው መሆኑም ተገልጿል።

የዓለም ባንክ ኃላፊ ዴቪድ ማልፓስስ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ የቀውሱን ሌላ ጎን ማየት ከባድ ነው ብለዋል።

አንዳንድ በማደግ ላይ ያሉ አገራት መንግሥታት እቃዎችን መግዛት አለመቻላቸውን እንዲሁም የብድር ዕዳ ውስጥ እየተዘፈቁ ነው ብለዋል ።

የባንኩ አዲስ የዓለም አቀፍ እድገት ትንበያ ከዜሮ በታች 2.9 በመቶ ሲሆን፣ ይህም በ80 ዓመታት ውስጥ ከፍተኛው መቀነስ የታየበት መሆኑን ቢቢሲ አስነብቧል።

@tikvahethiopia