#ጥንቃቄ

‘ US Embassy Addis Ababa ’ በሚል ስም ከ127 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የቴሌግራም ቻነል " አሜሪካ ኤምባሲ በጦርነት የተጎዳዉን የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለመደገፍና ከክፍለዘመን የዘለቀዉን የአሜሪካና የኢትዮጵያን ወዳጅነት ለማጠናከር ለ20 ሺህ ኢትዮጵያዉያን በአሜሪካ የስራ ዕድል ፈጥሯል " ብሎ መረጃ አጋርቷል።

የዕድለኞች የትራንስፖርት ፤ የመኖሪያ ቤትና የመኪና ወጪ በኤምባሲዉ እንደሚሸፈንም ጽፏል።

ስለዚህም የዕድሉ ተጠቃሚ መሆን የሚፈልጉ ኢትዮጵያዉያን በቴሌግራም ቻነሉ አማካኝነት እንዲመዘገቡና ተመዝጋቢዎችም ሙሉ ስማቸዉን፤ ስልክ ቁጥራቸዉን እንዲሁም አድራሻና መሰል ግላዊ መረጃዎቻቸዉን እንዲልኩም ይጠይቃል።

ይህን በተመለከተ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ እየተሰራጨ ያለድ መረጃ ሀሰተኛ እና ሰዎችን ለማጭበርበር እንደሆነ ገልጿል።

ኤምባሲዉ ለኢትዮጵያ ቼክ የመረጃ አጣሪ ድረገፅ በሰጠው ቃል፤ በአሜሪካ የስራና የቪዛ ዕድሎችን በተመለከተ በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገጾች #ሀሰተኛ መረጃዎች እየተጋሩ መሆኑን አስታዉቋል።

" የአሜሪካ መንግስት በኢሜይል፤ ፌስቡክ ሚሴንጀር፤ ቴሌግራም ወይም ሌላ ማህበራዊ ትስስር ገጾች አማካኝነት ግላዊ መረጃዎችን አይጠይቅም " ሲል ኤምባሲው አስረድቷል

ትክክለኛ የስራ ዕድሎችን በድረ-ገጹ ላይ እንደሚለጥፍና ሰዎች ለአጭበርባሪዎች እንዳይጋለጡ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ኤምባሲዉ ጠይቋል።

Via Ethiopia Check

@tikvahethiopia