#US

የአሜሪካው ፕሬዜዳንት በሀገራቸው ለሚታየው የዋጋ ግሽበት የሩስያን መሪ ቭላድሚር ፑቲንና የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ተጠያቂ አደረጉ።

ትላንት ጆ ባይደን ለሀገራቸው ህዝብ በሀገሪቱ የኢኮኖሚ ሁኔታ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በዚህ ማብራሪያቸው ለዋጋ ግሽበት የኮቪድ-19 ወረርሽኝንና ሩስያን ተጠያቂ አድርገዋል።

"ዛሬ እያየን ያለነው የዋጋ ንረት ሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች አሉ" ያሉት ባይደን አንደኛው አስከፊው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መሆኑን አስተዋል።

ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ "ፑቲን በዩክሬን ላይ የከፈተው ጦርነት ነው" ሲሉ ተደምጠዋል፤ ባይደን በመጋቢት ወር ከተመዘገበው የዋጋ ግሽበት 60% የሚሆነው ከነዳጅ የዋጋ ጭማሪ ጋር በተያያዘ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ባይደን ዩክሬንና ሩስያ በስንዴና በቆሎ ምርታቸው ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚይዙ በማስረዳት "የፑቲን ጦርነት የምግብ ዋጋ እንዲጨምር አድርጓል" ሲሉ የሩስያውን መሪያ ተጠያቂ አድርገዋል።

ከሪፖርተሮች በአሜሪካ ለሚታየው የዋጋ ግሽበት አስተዳደራቸው ኃላፊነት ይወስድ እንደሆነ ሲጠየቁ "ፖሊሲዎቻችን የሚያግዙ እንጂ የሚጎዱ አይመስለኝም" ሲሉ መልሰዋል።

ባይደን በሀገራቸው የሚታየው የዋጋ ግሽበት ሊፍታ የሚገበው ከፍተኛ ችግር መሆኑን በማንሳት ችግሩን ለመፍታት ልዩ ትኩረት አድርገው እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

ፕሬዜዳንቱ በትላንት ማብራሪያቸው "በእርግጥ የተወሳሰበ ነው። የአሜሪካ ዜጎች ሊረዱት እንደማይችሉ ግን እየጠቆምኩ አይደለም። እነሱ ይረዱታል፤ ጠረጴዛቸው ላይ ምግብ እንዲኖር ለማድረግ በቀን 8፣ 10 ሰዓታት እየሰሩ ነው" ብለዋል።

መቼ የምርቶች ዋጋ ይቀንሳል ለሚለው ባይደን ለመተንበይ ፍቃደኛ ሳይሆኑ የቀሩ ሲሆን የዋጋ ግሽበቱን ለመቆጣጠር ምን መስራት እንዳለብን እናውቃለን ብለዋል telegra.ph/US-05-11-2

@tikvahethiopia