#IMF

ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ፥ የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት የዓለም ኢኮኖሚ ዕድገትን ዝግ እንደሚያደርገው ትላንት ይፋ ባደረገው ሪፖርት አሳውቋል።

IMF ፤ የዓለም ምጣኔ ሀብት እ.አ.አ. ባለፈው 2021 በ6.1 ከመቶ ማደጉን አስታውሶ ዘንድሮ ግን ዕድገት የሚኖረው በ3.6 % ብቻ እንደሚሆን ተንብዩዋል።

" ጦርነቱ በምጣኔ ሀብት ላይ ያሳደረው አንድምታ ራቅ እያለም አድማሱንም እያሰፋ ነው " ሲል ገልጿል።

IMF የውጭ ንግድ የመሳሰሉ እንቅስቃሴዎችን በማስተጓጎል እንዲሁም የነዳጅ እና የምግብ ዋጋ ንረት በማስከተል የዓለም ኢኮኖሚ ወደ አሉታዊ አቅጣጫ እንዲያመራ አድርጓል ሲል አመልክቷል።

ዋናው የIMF ኢኮኖሚስት ፒየር ኦልቪዬ ጉሪንቻስ በጻፉት የዓለም ኢኮኖሚ ትንበያ ሪፖርቱ መግቢያ ፦

" በዓለም አቀፉ ወረርሽኝ ምክንያት ተንኮታኩቶ የነበረው የዓለም ኢኮኖሚ ጠንከር ብሎ ሊያንሰራራ ተቃርቦ ነበር።

ጦርነቱ መጣና በቅርብ ጊዚያት የተገኙ አብዛኞቹን ስኬቶች ጠራርጎ የሚያጠፋ ሁኔታ ፈጠረ።" ሲሉ ገልፀዋል።

በሌላ በኩል ፤ IMF ከዚህ ቀደም ለዓለም አገራት በሰራው ትንበያ የገደፈውን የኢትዮጵያን ምጣኔ ሐብት የተመለከቱ መረጃዎች በትላንት ሪፖርቱ አካቷል።

እኤአ 2022 የኢትዮጵያ ምጣኔ ሐብት 3.8 በመቶ ያድጋል ሲል ተንብዩዋል። በ2023 የኢትዮጵያ ኤኮኖሚ 5.7 በመቶ ያድጋልም ብሏል።

በሸማቾች የዋጋ ግሽበት መለኪያ (Consumer Prices) ባለፈው ዓመት በኢትዮጵያ 26.8 በመቶ የነበረው የሸቀጦች ዋጋ ንረት በተያዘው ዓመት ወደ 34.5 በመቶ እንደሚደርስ የIMF ትንበያ ያሳያል። ይኸ እኤአ 2023 በአንጻሩ 30.5 በመቶ ይሆናል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/IMF-04-20 (VOA, DW, IMF)

@tikvahethiopia