#Russia #Ukraine

ሰሞኑን አዲስ አበባ በሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ በር ላይ በርካታ " ኢትዮጵያዊያን ሩሲያን ወግነው ዩክሬንን ለመውጋት " ለመመዝገብ ወረፋ በመጠባበቅ ላይ ናቸው የሚል ምስል ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት እየተሰራጨ ነው።

ኢትዮጵያውያኑ በእጃቸው ላይ ዶክመት ይዘው ተሰልፈው ይታያል።

የሩስያ ኤምባሲ ፕረስ አታቼ የሆኑት ማሪያ ቸርኑኪና ለአል ዐይን በሰጡት ቃል ፤ " ሩሲያ ለዩክሬን ጦርነት ኢትዮጵያዊያንን ለመቅጠር ማስታወቂያ አላወጣችም፣ በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጨ ያለው መረጃም ሀሰተኛ ነው " ሲሉ መልሰዋል።

ነገር ግን ኢትዮጵያውን ወደ ኢምባሲው መሄዳቸው እውነት መሆኑን ገልፀዋል።

ኢትዮጵያውያን ወደ ሩሲያ ኢምባሲ የሄዱት ለምልመላ ሳይሆን ለሩሲያ ያላቸውን አጋርነት ለማሳየት መሆኑን ነው የገለፁት።

ይሁንና ሩሲያ ከዩክሬን ጋር እያደረገችው ባለው ጦርነት " በርካታ ኢትዮጵያዊያን በኢሜይል እና በአካል ከሩሲያ ጎን መሆናቸውን እያሳወቁን ነው ለዚህ እናመሰግናለን " ሲሉም አክለዋል።

ኢትዮጵያዊያን ይሄንን እያደረጉ ያለው ረጅም እና ታሪካዊ በሆነው የኢትዮጵያ እና ሩሲያ ወዳጅነት ላይ ስለሚተማመኑ እንደሆነ ኤምባሲው ተገልጿል።

የዩክሬን ኤምባሲ ደግሞ ሩስያ ምልመላ እያደረገች ነው በሚል የተሰራጨውን መረጃ በተመለከተ ለኢትዮጵያ ቼክ መረጃ ማጣሪያ ድረገፅ በሰጠው ቃል ፤ "ይህ አሳዛኝ ድርጊት ነው። አንድ ኢትዮጵያዊ በዚህ ጦርነት ህይወቱ ቢያልፍ ለዩክሬንም ሆነ ለኢትዮጵያ አሳዛኝ ክስተት ይሆናል። " ብሏል።

መረጃው የአል ዓይን ኒውስ እና የኢትዮጵያ ቼክ የመረጀ ማጣሪያ ድረገፅ ነው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT