#BREAKING

ሩስያ በአምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሂውማን ራይትስ ዎች ላይ እርምጃ ወሰደች።

ከተመድ የሰብዓዊ መብቶች ም/ቤት የታገደችው እና በዩክሬን የጦር ወንጀል ፈፅማለች እየተባለች በሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ስሟ እየተነሳ ያለው ሩስያ ላለፉት 30 ዓመታት በሀገሪቱ ሲንቀሳቀሱ የነበሩትን ሁለቱን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች (ሂውማን ራይትስ ዎች እና አምነስቲ ኢንተርናሽናል) ፤ የምዝገባ ፍቃድ ሰርዛለች በሀገሯ (ሞስኮ) የነበሩ ቢሮዎችን ዘግታቸዋለች።

ሩስያ ከአምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሂውማን ራይትስ ዎች ባለፈ በአጠቃላይ 15 ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት (NGO)ን " ዝርዝር ማብራሪያ ሳትሰጥ " የሩስያ ፌዴሬሽን ህግን በመጣስ " በሚል እርምጃ እንደተወሰደባቸው በፍትህ ሚኒስቴሯ በኩል አሳውቃለች።

@tikvahethiopia