#SouthSudan

የጎረቤታችን የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ የፖለቲካ እና ወታደራዊ ኃይሎች በመካከላቸው የነበረውን የተካረረ መቃቃር ለመፍታት በዋና ከተማቸው ጁባ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነት ላይ የደረሱት በሌላኛዋ ጎረቤታችን ሱዳን አሸማጋይነት ነው።

የፖለቲካ ኃይሎቹ የተካረረ መቃቃር ውስጥ ገብተው ነበር የተባለ ሲሆን ይህንን ችግር ለመፍታት ተስማምተዋል።

ስምምነቱ ከሁሉም የተውጣጣና ጠንካራ ብሔራዊ ጦርን ለመመስረት የሚያስችል ሲሆን ይህን ለማጽናት የሚያስችል ሰነድ ተዘጋጅቶም ተፈራርመዋል፡፡

ፊርማው የፓለቲካ ኃይሎቹን የማሸማገሉን ሚና በወሰዱት የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ጄ/ል መሃመድ ሃምዳን ደገሎ በተገኙበት የተፈረመ ነው።

ለመገንባት በታሰበው ብሔራዊ ጦር ወጥነት ያለው እዝን ለመፍጠርና ስልጣን ለመከፋፈል እንደሚያስችል ተነግሮለታል።

ጄ/ል መሃመድ ሃምዳን ደገሎ (ሄሜቲ) ፥ " በፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር እና በምክትላቸው ሬይክ ማቻር (ዶ/ር) በሚመሩ ኃይሎች መካከል የተፈጠረውን መቃቃር በማርገብ ለማስማማት ያደረግነው ጥረት ተሳክቶልናል " ያሉ ሲሆን " ወንድሞቻችን የሃገራቸውን ሰላምና ደህንነት ለማስቀጠል በሚያስችል ትክክለኛ መንገድ ላይ በመገኘታቸው ደስተኞች ነን " ሲሉ መሪዎቹን አመስግነዋል፡፡

(አል ዓይን ኒውስ)

@tikvahethiopia