TIKVAH-ETHIOPIA
#ማስታወሻ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመርያ መሠረት ባንኮች የደንበኞቻቸውን የተሟለ መረጃ እንዲያጠናክሩ የተሰጣቸው የጊዜ ገደብ በዚህ ሳምንት ይጠናቀቃል። ከተሰጠው ቀነ ገደብ በኋላ መረጃዎችን ያልሰጡ ደንበኞች አካውንታቸውን #ማንቀሳቀስ አይችሉም። ባንኮች ባለፉት 6 ወራት መመርያው በሚጠይቀው መሥፈርት መሠረት የደንበኞቻቸውን መረጃ እየሰበሰቡ ነው፡፡  ይህንኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመርያ ተከትለው…
#NBE

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመርያ መሠረት ባንኮች የደንበኞቻቸውን የተሟለ መረጃ እንዲያጠናክሩ የተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ባለፈው የካቲት 20 ቀን 2014 ተጠናቋል።

መረጃዎችን ያልሰጡ የባንክ ደንበኞች አካውንታቸውን #ማንቀሳቀስ እንዳይችሉ ሆነዋል (በሚሊዮን ሊቆጠሩ ናቸው ተብሎ ይታመናል) ፤ አካውንታቸውን ማንቀሳቀስ የሚችሉትም በመመሪያው መሰረት መረጃ ሲሰጡ ብቻ ነው።

የ " መታወቂያ እድሳት " ግን እንቅፋት የሆነባቸው ብዙ ናቸው ለእነሱ የታሰበ ነገር ስለመኖሩ የታወቀ ነገር የለም።

ባንኮች ደንበኞቻቸው መረጃ እንዲሞሉ ላለፉት 6 ወራት ያህል በዋና ዋና ሚዲያዎች፣ በማህበራዊ ሚዲያ ፣ በአጭር የፅሁፍ መልዕክት ፣ በባንኮች የማስታወቂያ ቦርድ ላይ ጥሪ ሲያቀርቡ የነበረ ሲሆን አንዳንድ ባንኮች በመጨረሻው ሳምንት በስልክ እየደወሉ ለመቀበል ጥረት አድርገዋል።

ከቀነገደቡ መጨረሻ በፊት የባንክ ኃላፊዎች በመመርያ የተደነገገውን ማስፈጸም ከባድ ሥራ በመሆኑ መረጃ የማሰባሰቡ ሥራ ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገዋል የሚል አስተያየት ቢሰጡም ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምላሽ ሳይሰጥ ጊዜው አልቋል።

በዚሁ አጋጣሚ በተለይ በማህበራዊ ሚዲያ የግጭት ፣ የጥላቻ መልዕክቶች፣ ፌዝ ፣ ስድብ እና አሉታዊ ነገሮች ለብዙሃን በፍጥነት እና በብዛት ሼር ከማድረግ ይልቅ ወሳኝ ጠቃሚ መልዕክቶች የማጋራት ልምድና ኃላፊነት ሊጨምር ይገባል።

ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ጠቃሚ መልዕክቶችን በአግባቡ ብናጋራ መረጃ ላልሰማው ወገናች እንዲሰማ እንዲሁም ደግሞ በመጨረሻ ቀናት ከሚፈጠር ወከባ ብዙ ሰዎችን መካከል ይቻላል።

@tikvahethiopia