#DrAbiyAhmed

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ በአራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ እረፍት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ " አራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ማረፋቸውን በመስማቴ ጥልቅ ኀዘን ተሰምቶኛል። " ብለዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ፥ ተለያይተው የነበሩት ሁለቱ ሲኖዶሶች አንድ እንዲሆኑ ቅዱስነታቸው ወሳኙን ሚና መጫወታቸውን አስታውሰዋል።

" ነገሮችን በአርምሞ እየተመለከቱ ሀገራችንን በጸሎት ያግዙ ነበር። " ያሉት ጠቅለይ ሚኒስትሩ " በዚህ ወቅት እርሳቸውን ማጣት ከባድ ጉዳት ነው። ለሁላችንም መጽናናትን እመኛለሁ " ብለዋል።

@tikvahethiopia