TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በአንደኛው ዙር በፀጥታ ችግር የ12ኛ ክፍል ፈተና መውሰድ ያልቻሉ ተማሪዎች ዛሬ ፈተናቸውን ጀምረዋል። መልካም ፈተና! @tikvahethiopia
#Update

የመጀመሪያው ቀን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ሲሰጥ ውሏል።

ፈተናው በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ አፋር እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ተሰጥቷል።

#Amahra

በአማራ ክልል ከ37 ሺ በላይ ለሆኑ ተማሪዎች ዛሬ ፈተና ሲሰጥ ውሏል። ፈተናው በደቡብና ሰሜን ወሎ፣ ዋግኸምራ፣ ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞኖችና በደሴ ከተማ ፣ የሰሜን ሸዋ ዞን 3 ወረዳዎች፣ በሰሜን ጎንደር ዞን በ1 የፈተና ጣቢያ ፈተናው ነው የተሰጠው።

በሌላ በኩል ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች ተፈናቅለው ለመጡ 220 ተማሪዎችም በልዩ ሁኔታ በቡሬ በተቋቋመ የመፈተኛ ጣቢያ ተፈትነዋል።

#OromiaRegion

በኦሮሚያ ክልል በቄለም ወለጋ ዞን በ12 ወረዳዎች በ42 የፈተና ጣቢያዎች 14,228 ተማሪዎች ለፈተና መቀመጣቸው ፤ ፈተናውን እንደሚወስዱ ከተጠበቁት 16,608 ተማሪዎች መካከል 1, 243 በተለያዩ ምክንያቶች ፈተና ላይ አለመቀመጣቸው ተገልጿል።

በምዕራብ ወለጋ የቤጊ እና ቆንደላ ወረዳዎች 1,137 ተማሪዎች በአራት የፈተና ጣቢያ ፈተናው ላይ የተቀመጡ ሲሆን በተለያዩ ምክንያቶች 931 ተማሪዎች ፈተናው ላይ እንዳልተቀመጡ ተገልጿል።

#Afar

በአፋር ክልል ፈተናውን ይወስዳሉ ተብለው ከተጠበቁት 257 ተማሪዎች 154 ተማሪዎች ፈተናውን መውሰድ ጀምረዋል።

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን አንፃራዊ ሠላም ተመዝግቦባቸዋል በተባሉ አካባቢዎች የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ሲሰጥ ውሏል።

• የሁለተኛው ቀን ፈተና ይቀጥላል።

መረጃ ፦ ኢብኮ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ፣ የአማራክ ክልል ትምህርት ቢሮ

ፎቶ ፦ የደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ የወልዲያ ከተማ ፣ የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ቢሮዎች ፣ የቤ/ጉ ክልል ትምህርት ቢሮ

@tikvahethiopia