#ማሳሰቢያ

በአዲስ አበባ የኮቪድ 19 ስርጭትን ለመግታት በትራንስፖርት ዘርፍ የወጡ የመከላከያ መንገዶች በአግባቡ እንዲተገበሩ የአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ቢሮ አሳስቧል።

ቢሮው ዛሬ በትራንስፖርት ዘርፍ የኮቪድ 19 ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የቫረሱን ስርጭት ለመቀነስ በትራንስፖርት ዘርፍ የተቀመጠውን መመሪያ ተግባራዊ በማያደርጉ አሽከርካሪዎች ላይ ከዛሬ ጀምሮ ቁጥጥር እንደሚደረግ ተገልጿል።

የትራንስፖርት አገልግሎት በሚሰጥበት ወቅት፦
- የተሽከርካሪዎችን ንጽህና መጠበቅ፣
- አሽከርካሪዎችና ረዳቶች ማስክ መጠቀም
- ማስክ ያላደረጉ ተሳፋሪዎች አገልግሎት እንዳያገኙ ማድረግ እንደሚገባም ተብራርቷል፡፡

የኮቪድ ስርጭት ለመግታት በወጣው መመሪያ መሰረት ማስክ ያላደረጉ አሽከርካሪዎች እና ረዳቶች ከተገኙ ብር 1 ሺህ የሚያስቀጣ ሲሆን፥ ማስክ ያላደረጉ ተሳፋሪ በሚጭኑበት ወቅት በአንድ ሰው 500 ብር የሚያስቀጣ ይሆናል፡፡

ምንጭ፦ የአ/አ ትራንስፖርት ቢሮ

@tikvahethiopia