TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ኮሎኔል ማማዲ ዱምበያ ስለብሄራዊ ቡድኑ ምን አሉ ?

የጊኒ ብሄራዊ ቡድን በካሜሮን የ2021 አፍሪካ ዋንጫ በጊዜ ከተሰናበቱት ሀገራት መካከል እንደምትገኝበት ይታወቃል።

ቡድኑ ወደ ካሜሮን በተሸኘበት ምሽት አሁን ጊኒን እያስተዳደር ያለው የጁንታ መሪ ኮሎኔል ማማዲ ዱምበያ ለቡድኑ አባላት ያስተላለፉት መልዕክት መነጋገሪያ ሆኖ እንደነበር የሁላችንም ትውስታ ነው።

ኮሎኔል ማማዲ ዱምበያ የሀገሪቱን ባንዲራ 🇬🇳 ለቡድኑ ካስረከቡ በኃላ ባስተላለፉት መልዕክት የቡድኑ አባላት ዋንጫውን ይዘው እንዲመጡ ካልሆነ ግን በእነሱ ላይ ኢንቨስት የተደረገውን እያንዳንዱን ገንዘብ እንዲመልሱ /እንዲተኩ ነበር ያሉት።

ቡድኑም በአፍሪካ ዋንጫው ሳይሳካለት ቀርቶ በጊዜ ተሰናብቷል ፤ ይህን ተከትሎ የጁንታውን መሪ ኮሎኔል ማማዲ ዱምበያ አስተያየት ብዙዎች ሲጠብቁት ነበር።

ኮሎኔል ማማዲ ዱምበያም ዝም አላሉም።

ኮሌኔሉ ብሄራዊ ቡድኑን 'ይቅር' እንዳሉ ገልፀው ፤ በወቅቱ ያን ንግግር የተናገሩት ቡድኑን ለማበረታታ ብቻ መሆኑ አሳውቀዋል። " የቡድን ግንባታ ጊዜ እንደሚወስድ እገነዘባለሁም " ብለዋል።

ነገር ግን ለቡድኑ የተሰጠው ገንዘብ ሩብ ፍፃሜ ፣ ግማሽ ፍፃሜ እና የፍፃሜ ጨዋታዎችን የሚሸፍን ሲሆን ያ ገንዘብ ወደ መንግስት ካዝና ይመለሳል ተብሏል።

@tikvahethiopia