#SouthSudan

ደቡብ ሱዳን ከምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት የልማት ባለስልጣን /ኢጋድ/ አባልነት ታግዳለች።

ኢጋድ ከአባልነት ያገዳት በየዓመቱ ለተቋሙ መክፈል የሚጠበቅባትን መዋጮ ባለመክፈሏ ነው።

የደቡብ ሱዳን የማስታወቂያ፣ የመገናኛ እና የፖስታ አገልግሎት ሚኒስትር ሚካኤል ማኩዌ ሀገራቸው በተባለው ምክንያት ከኢጋድ መታገዷ አረጋግጠዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትሩ ማይክ አዪ ድንግ በካቢኔ ስብሰባው ላይ ለኢጋድ መዋጮ ሚሆን ገንዘብ መጠየቃቸውን አስታውቀዋል።

ካቢኔው ከመከረ በኋላ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከአዲሱ የገንዘብ ሚኒስትር ጋር እንዲወያዩበት መወሰኑን ገልፀዋል።

ይህም ሁሉንም ውዝፍ ለመክፈል የሚያስችል መንገድ የሚያመቻች ነው ብለዋል።

ምንጭ፦ አልዓይን / ሲጂቲኤን

@tikvahethiopia