TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በታህሳስ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተደርጓል። በዚህ መሰረት ፦ • ቤንዚን ባለፈው ወር ሲሸጥበት ከነበረው ዋጋ ጭማሪ በማድረግ በሊትር 31 ብር ከ74 ሳንቲም እንዲሸጥ ተወስኗል። • ነጭ ናፍጣ 28 ብር ከ94 ሳንቲም፣ • ነጭ ጋዝ 28 ብር ከ94 ሳንቲም፣ • ቀላል ጥቁር ናፍጣ 23 ብር ከ73 ሳንቲም፣ • ከባድ ጥቁር ናፍጣ 23 ብር ከ29 ሳንቲም …
' የቤንዚን ዋጋ 31 ብር ከ74 ሳንቲም ነው '

አንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች በታህሳስ ወር የነዳጅ ምርቶች ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ በተደረገው ማስተካከያ የቤኒዚን ዋጋ 34 ብር ከ71 ሳንቲም በማለት እያሰራጩት ያለው መረጃ #ስህተት ነው።

በተደረገው የታህሳስ ወር ማስተካከያ የቤንዚን ዋጋ 31 ብር ከ74 ሳንቲም ነው እንዲሸጥ የተወሰነው።

በሌላ በኩል ከዚህ ቀደም የነበሩት ወራት የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ምን እንደሚመስል መለስ ብለን እንመልከት።

ከየካቲት 27/2013 ዓ/ም እስከ መጋቢት 30/2013 ዓ/ም በነበረው የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ (በሊትር) የነበረው ፦

• ቤንዚን 👉 25 ብር ከ86 ሳንቲም
• ኢታኖል ድብልቅ ቤንዚን 👉 25.36 ሳንቲም
• ነጭ ናፍጣ 👉 23 ብር ከ18 ሳንቲም
• ኬሮሲን 👉 23 ብር ከ18 ሳንቲም
• ቀላል ጥቁር ናፍጣ 👉 20 ብር ከ27 ሳንቲም
• ከባድ ጥቁር ናፍጣ 👉 19 ብር ከ78 ሳንቲም
• የአውሮፕላን ነዳጅ 👉 38 ብር ከ60 ሳንቲም ነበር።

ከዚህ በኃላ ፦

🗓ከመጋቢት 26 እስከ ሚያዚያ 30/2013 ዓ/ም ከአውሮፕላን ነዳጅ ውጭ ሁሉም ባለበት ቀጥሏል።

🗓ከሚያዚያ 28 እስከ ግንቦት 28/2013 ዓ/ም ከአውሮፕላን ነዳጅ ውጭ ሁሉም ባለበት ቀጥሏል።

🗓ከግንቦት 28 እስከ ሰኔ 30/2013 ዓ/ም ከአውሮፕላን ነዳጅ ዋጋ ውጭ ሁሉም ባለበት ቀጥሏል።

🗓ከሰኔ 30 እስከ ሀምሌ 30/2013 ዓ/ም ከአውሮፕላን ነዳጅ ውጭ ሁሉም ባለበት ቀጥሏል።

🗓ከነሃሴ 1 እስከ ነሃሴ 30/2013 ዓ/ም ከአውሮፕላን ነዳጅ ውጭ ሁሉም ባለበት ቀጥሏል።

🗓ከጳጉሜ 1 እስከ መስከረም 30/2014 ዓ/ም የአውሮፕላን ነዳጅ ዋጋ ጨምሮ ሁሉም ባለበት ቀጥሏል።

🗓ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 30/2014 ዓ/ም ከአውሮፕላን ነዳጅ ዋጋ ውጭ ሁሉም ባለበት ቀጥሏል።

🗓ከጥቅምት 30 እስከ ህዳር 30/2014 ዓ/ም ከአውሮፕላን ነዳጅ ዋጋ ውጭ ሁሉም ባለበት ቀጥሏል።

በታህሳስ ወር በተደረገው ማስተካከያ ደግሞ ፦

• ቤንዚን 👉 31 ብር ከ74 ሳንቲም
• ነጭ ናፍጣ 👉 28 ብር ከ94 ሳንቲም፣
• ነጭ ጋዝ 👉 28 ብር ከ94 ሳንቲም፣
• ቀላል ጥቁር ናፍጣ 👉 23 ብር ከ73 ሳንቲም፣
• ከባድ ጥቁር ናፍጣ 👉 23 ብር ከ29 ሳንቲም
• የአውሮፕላን ነዳጅ 👉 58 ብር ከ77 ሳንቲም እንዲሸጥ ተወስኗል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህን መረጃ ያሰባሰበው ከዚህ ቀደም በንግድ እና ኢንዲስትሪ ሚኒስቴር በኩል ይፋ የተደረጉትን የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ወደኃላ ተመልሶ በመመልከት ነው።

NB : ከጥቅምት ወር 2014 ዓ/ም ጀምሮ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ በተመለከተ ይፋ እየተደረጉ ያሉት በአዲሱ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በኩል ነው።

@tikvahethiopia