TIKVAH-ETHIOPIA
#AmbassadorTayeAtskeSelassie ትላንት በነበረው የተመድ ፀጥታው ምክር ቤት ስበስባ ላይ ኢትዮጵያን በመወከል አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ንግግር አድርገው ነበር። አምባሳደር ታዬ በህወሓት የተፈጸመው የክህደት ስራ በእጅጉ የሚያሳዝንና ኢትዮጵያ በዚህ ወንጀለኛ ቡድን ያሳለፈችውን ጊዜ ለመርሳት የአንድ ትውልድ ጊዜ የሚፈጅ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ቡድኑ ያን ሁሉ ደም መፋሰስ እንዲፈጠር ባያደርግ…
#UNSC

በትላንትናው የፀጥታው ምክር ቤት ሰብሰባ ላይ የሀገራት ተወካዮች ምን አሉ ?

#ኢትዮጵያ ፦

የኢትዮጵያ መንግስት ባለፈው አንድ (1) ዓመት ከህወሓት የተቃጣበትን ወታደራዊ አደጋ መመከቱን አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ተናግረዋል።

መንግሥት ምግብን ጨምሮ ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶችን በትግራይ ክልል የሰብአዊ እርዳታ ለሚፈልጉ ሰዎች ከUN ጋር በመተባበር ሲያቀርብ እንደነበር ተናግረዋል።

ለሰብአዊ ድጋፍ እንዲያመች በሚል የተናጠል የተኩስ አቁም ማድረጉን ተናግረዋል። ነገር ግን የተደረገው ጥረት ሁሉ በወንጀለኛው ቡድን ምክንያት ከንቱ ሆኖ ቀርቷል ብለዋል።

"በዚህ የወንጀል ቡድን ምክንያት የትግራይ ክልል ሕዝብ ያስፈልገው የነበረውን አስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታ እያገኘ አይደለም" ሲሉ ለምክር ቤቱ አስረድተዋል።

በአማራ ክልል እና በአፋር ክልል በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ሰዎችም በዚህ ቡድን በየበራቸው ላይ መገደላቸውን ገልጸዋል።

#ቻይና ፦

ቻይናን የወከሉት ዣንግ ጁን ኢትዮጵያ ውስጥ እየተከሰተ ያለው ሁኔታ የፖለቲካ፣ የታሪክ፣ የብሔርና ሌሎች ምክንያቶች ጥምር ውጤት መሆኑን ጠቁመው መፍትሔ የሚገኘው በአገር ውስጥ ብቻ መሆኑን ተናግረዋል።

የአፍሪካን ችግሮች ለመፍታት አፍሪካዊ መፍትሄዎች ለማግኘት ለሚደረገው ጥረት በድጋሚ ድጋፍ እንሰጣለን ብለዋል።

በተለይ አሜሪካና የተለያዩ አገራት የሚያደርጉትን ማዕቀብ በተመለከተም አስተያየታቸውን የሰጡት ተወካዩ፣ በንግድ ላይ ገደብ ማድረግ እና እርዳታን ማቋረጥ በፖለቲካው መፍትሄ ላይ ጣልቃ መግባት እንደሆነ አስረድተዋል።

ለፀጥታው ምክር ቤት አባላት ምክራቸውን ያስተላለፉት የቻይናው ተወካይ አባል አገራቱ የአገሪቱን ሉዓላዊነትና አመራር በማክበር ኢትዮጵያ የሰብአዊ አቅሟን እንድታሻሽል እና የሚሰጠው እርዳታም ሊጨምር ይገባል ብሏል።

#አሜሪካ ፦

አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ 1 አመት ባስቆጠረው ግጭት ውስጥ ለተፈጠሩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ፥ "ሁሉም ኃሃይሎች ጥፋተኞች ናቸው፤ ጥፋት የለሌለበት የለም" ሲሉ ተናግረዋል።

አምባሳደር ሊንዳ የህወሓት ታጣቂዎች በአማራ ክልል እና አፋር ክልል እንዲወጡ እና ጥቃታቸውን ወደ አዲስ አበባ እንዳያሰፉ አሳስበዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ዓለም አቀፍ የጦርነት ሕጎችን እንዲሁም የሰብአዊ መብት ሕጎችን እንዲያከብር ጠይቀዋል።

ሰላምን ሊያመጡ የሚችሉት ኢትዮጵያዊያን ብቻ ናቸው ሲሉም አምባሳደሯ ተናግረዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/UNSC-11-09