#ItsMyDam🇪🇹

" የተርባይኖቹ ሃይል ማመንጨት ተከዜና ጣና በለስ ግድቦችን በአንድ ጊዜ የማጠናቀቅ ያህል ነው " - ፕሮፌሰር ይልማ ስለሺ

የታላቁ የህዳሴ ግድብ 2 ተርባይኖች ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት መጀመር ተከዜንና ጣና በለስ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድቦችን በአንድ ጊዜ የማጠናቀቅ ያህል መሆኑን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ተደራዳሪ አባል ፕሮፌሰር ይልማ ስለሺ ገለጹ።

ፕሮፌሰር ይልማ ስለሺ ለኢፕድ በሰጡት ቃል ፥ በጣና በለስና በተከዜ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድቦች የሚመረተው የኤሌክትሪክ ሃይል የህዳሴው ግድብ ሁለቱ ተርባይኖች ከሚመነጩት ኤሌክትሪክ ሃይል እኩል ነው ብለዋል።

ሁለቱ ተርባይኖች ተጠናቀው ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት መጀመር ሁለት ግዙፍ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድብ ፕሮጀክቶች በአንድ ጊዜ እንደማጠናቀቅ ይቆጠራል ሲሉም ገልፀዋል።

ፕሮፌሰሩ ፥ ጣና በለስና ተከዜ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድቦች እንደቅደም ተከተላቸው 460ና 300 ሜጋ ዋት ሃይል እንደሚያመነጩ አውስተው፤ የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሃይል ማመንጫ ግድብ ሁለት ተርባይኖች ስራ መጀመር 750 ሜጋ ዋት ሃይል ስለሚያመነጩ ሁለት ትልልቅ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድቦችን የማጠናቀቅ ያህል ነው ብለዋል።

Credit : EPA

@tikvahethiopia