#Bahridar : በባህር ዳር ከተማ እየተገነባ የሚገኘውን የአባይ ድልድይ የግንባታ ብረት የሰረቁት ግለሰቦች በቁጥጥር ዋሉ።

ከ50 ዓመት በላይ አግልግሎት የሰጠው የባህርዳር ከተማ አባይ ድልድይ በእድሜ ብዛት ወቅቱን የሚመጥን የትራፊክ ፍሰትን ማስተናገድ ተቸግሯል።

ይህንን ለመቅረፍ በከፍተኛ በጀት አዲሱ ድልድይ በአባይ ወንዝ ላይ እየተገነባ ነው።

የባህር ዳር ከተማ ፖሊስ ፥ "ይህንን የህዝብ ሀብት ለግል ጥቅም ማዋል የፈለጉ ስግብግብ ግለሰቦች የተለያዩ የስርቆት ወንጀል መፈፀማቸውን ተረጋግጧል" ብሏል።

በአካባቢው ቅኝት ሲያደርጉ የነበሩት የሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ ባልደረቦች በ12/02/2014 ዓ/ም ምሽት የድልድዩን የግንባታ ብረት ሰርቀው ሊያጓጉዙ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርምራ እያጣራ ይገኛል ሲልም አክሏል።

አጠቃላይ በስርቆቱ የተሳተፉ እና በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦች ግን በፖሊስ መረጃ ላይ አልተገለፀም።

የባህር ዳር ፖሊስ ፥ " ክልሉ የህልውና ትግል ላይ ባለበት በዚህ ወቅት የሀገርንና የህዝብን ሃብት በመዝረፍ ለግል ጥቅም ለማዋል የሚጥሩትን የውስጥ ባንዳዎች ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት ህብረተሰቡ የበኩሉን ሊወጣ ይገባል" ሲል ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia