TIKVAH-ETHIOPIA
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የስራ ርክክብ አደረጉ፡፡ በአዲሱ የመንግስት ምስረታ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከቀድሞ የትምህርት ሚኒስትር ጋር የስራ ርክክብ አድርገዋል፡፡ ለአዲሱ ሚኒስትር የቀድሞ የትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ በርክክቡ ወቅትም…
የትምህርት ሚኒስትሩ ከሰራተኞች ጋር ውይይት አካሄዱ።

በዛሬው ዕለት የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከሚኒስቴሩ አጠቃላይ ሰራተኞች ጋር ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል።

ውይይቱ በቀጣይ በትኩረት ሊሰሩ በሚገቡ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር ተብሏል።

ሰራተኞቹ በትምህርት ሚኒስቴር ውስጥ አሉ ያለቱን የአሰራር ፣ የመልካም አስተዳደር እና የአደረጃጀት ችግሮች ለሚኒስትሩ አሳውቀዋል።

በቀጣይም ሚኒስትሩ በተቋም ውስጥ ያሉትን ችግሮች በመፈተሽ መፍትሄ የመስጠት እና የትምህርት ሴክተሩን ከፓለቲካ እና ከንግድ ነፃ ለማድረግ ሊሰሩ እንደሚገባ ሰራተኞቹ ገልፀዋል።

ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ፥ በሰራተኞች የተነሱትን ሀሳቦች እንደ ግብዓት በመውሰድ እና መፍትሄ በመስጠት በቅንጅት የተሻለ ስራዎችን ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ፥ " የትምህርት ሴክተሩ የፓለቲካ መስሪያ ቤት ሳይሆን ህዝብን ለማገልገል የተቋቋመ ሴክተር በመሆኑ የፓሊቲካ አመለካከታችንን ትተን ስራዎች ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል " ሲሉ ተናግረዋል።

አክለውም፥ "ሚኒስቴሩ የተሻለ ትውልድ ለመፍጠር ከፍተኛ ሀላፊነት ያለበት ተቋም በመሆኑ የተሻለ ስራ መስራት ይጠበቅበታል " ብለዋል።

መረጃው ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia