" ባንክ ኦፍ አዲስ / Bank of Addis "

በ10 ቢሊዮን ብር በተመዘገበ ካፒታል አዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም ወደ ባንክ ማደጉ ተገለፀ።

አዲስ ብድር እና ቁጠባ ተቋም በ3.7 ቢሊዮን የተከፈለ እና በ10 ቢሊዮን ብር በተመዘገበ ካፒታል " ባንክ ኦፍ አዲስ " በሚል ወደ ባንክ ማደጉን የተቋሙ ማኔጅንግ ዳይሬክተር አቶ ዳምጠው አለማየሁ አስታውቀዋል።

የተቋሙ አመራሮችና ባለአክሲዮኖች ትላንት ጉባኤ ያካሄዱ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ መመሪያ መሰረት በማድረግ ወደ ባንክ እንዲሸጋገር መወሰናቸው ተገልጿል።

ወደ ባንክ የተሸጋገረው ተቋሙ ከሌሎች ባንኮች በተለየ ሁኔታ ጣምራ አገልግሎትን ለህብረተሰቡ ለመስጠት ያስችላል ተብሏል።

የአዲስ ብድር እና ቁጠባ ተቋም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ከመደበኛ ባንኮች የፋይናንስ አገልግሎት ማግኘት ለማይችሉ የህብረተሰብ ክፍሎች አዲስ አበባ ከተማ የስራ እድል ፈጠራ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ተብሎ በ1988 ዓ.ም በ5 አክሲዮኖች በ517 ሺህ ብር የተከፈለ ካፒታል እና ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ በተመዘገበ ካፒታል ነበር የተመሰረተው።

Credit : AAPS

@tikvahethiopia