* ኒውዮርክ

የኢትዮጵያ ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ መከሩ።

በኒውዮርክ የተመድ ስብሰባ እየተካፈሉ የሚገኙት አቶ ደመቀ፥ ከሀገራት ባለስልጣናት እና ከተቋማት አመራሮች ጋር የሚያደርጉት የጎንዮሽ ምክክር የቀጠለ ሲሆን ትላንት ከአንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር መክረዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይፋ ባደረገው መረጃ ዋና ፀሐፊው እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ በተለይም በትግራይ ውስጣዊ ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።

ዋና ፀሐፊው ወደ ሰላም የሚወስዱ እርምጃዎች እንዲኖሩ በድጋሚ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን የሰብአዊ ተደራሽነትን ይበልጥ ማመቻቸት አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በሌላ በኩል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በተመለከተ ዋና ፀሐፊው ውይይቱን እንደገና ማስጀመርን አስፈላጊ እንደሆነ አስገንዝበው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለአፍሪካ ህብረት የማሸማገል ጥረቶች ድጋፉን እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል።

@tikvahethiopia