#CHINA  đŸ‡¨đŸ‡ł #ETHIOPIA 🇪🇹

በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ለሚገኙ እና ይበልጥ ለኮቪድ-19 ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚሆን 300 ሺህ ዶዝ የኮቪድ-19 ክትባት ቻይና ለገሰች።

በዛሬው እለት ክትባቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዥያዎ ዢዮዋን ለዶክተር ሊያ ታደሰ አስረክበዋል።

በርክክቡ ወቅት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ እንደተናገሩት ይህ ከቻይና መንግስት ለሶስተኛ ግዜ ድጋፍ የተደረገው 300 ሺህ ዶዝ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት በዋናነት በስራቸው ይበልጥ ተጋላጭ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች በተለይም በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ይውላል ብለዋል፡፡

በተጨማሪ ድጋፉ ካለው የኮቪድ-19 ህሙማን መብዛትና የኮቪድ-19 ስርጭት መበራከት ጋር ተያይዞ ያለውን ጫና ከመቀነስ አንጻር ጉልህ ሚና ይጫወታል ብለዋል።

ቻይና  đŸ‡¨đŸ‡ł በዛሬው ዕለት የላከችውን 300 ሺህ ዶዝ ክትባትን ጨምሮ ለኢትዮጵያ 1 ሚሊየን ዶዝ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ድጋፍ አድርጋለች፡፡

#MoHEthiopia

@tikvahethiopia